የባቱ-አርሲ ነገሌ የፍጥነት መንገድ በሚያዝያ ወር አገልገሎት እንደሚጀምር ተገለፀ
17:06 30.10.2025 (የተሻሻለ: 17:14 30.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የባቱ-አርሲ ነገሌ የፍጥነት መንገድ በሚያዝያ ወር አገልገሎት እንደሚጀምር ተገለፀ
202 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው እና 3ኛው ምዕራፍ የሞጆ-ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ አሁን ላይ 95 በመቶ መጠናቀቁ ተገልጿል።
"ሙሉ በሙሉ ሥራ ለመጀመር የሚያስፈልገው ዘመናዊ የትራንስፖርት ሥርዓቶችን፣ የክፍያ ጣቢያዎችን እና የትራፊክ ምልክቶችን መትከል ብቻ ነው የቀረው" ሲሉ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሞጆ-ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አዲስህይወት ታደሰ ተናግረዋል።
የሞጆ-ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ በተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ድጋፍ በአራት ምዕራፍ የተከፋፈለ ነው፡፡
የፍጥነት መንገዱ የካይሮ-ኬፕ ታውን ትራንስ-አፍሪካ ሀይዌይ ወሳኝ ክፍል ሲሆን የድንበር ተሻጋሪ ትስስርን እና የአቅርቦት ሰንሰለት ቅልጥፍናን በማሻሻል፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ግቦችን በመደገፍ የኢትዮጵያን ክልላዊ ንግድ እና የሎጂስቲክ አቅም በእጅጉ ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X