የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አርቲ እና ስፑትኒክን ከውስጣዊ አውታረ መረቡ ሊያግድ እንደሆነ ዘገባዎች ጠቆሙ
15:47 30.10.2025 (የተሻሻለ: 15:54 30.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አርቲ እና ስፑትኒክን ከውስጣዊ አውታረ መረቡ ሊያግድ እንደሆነ ዘገባዎች ጠቆሙ
የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮበርታ ሜትሶላ ስፑትኒክ፣ አርቲ እና ሌሎች እገዳ የተጣለባቸው የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን የፓርላማውን አውታረ መረብ እና መሳሪዎች እንዳይጠቀሙ የሚከለክል ሃሳብ እያጤኑ እንደሆነ ፖለቲኮ ዘግቧል፡፡
በላትቪያ የፓርላማ አባል ሪሃርድስ ኮልስ የሚመራው ይህ ተነሳሽነት፤ ውስጣዊ የመግቢያ ደንቦችን ከቀሪ የአውሮፓ ህብረት ማዕቀቦች ጋር ለማጣጣም ያለመ ነው፡፡
ነገር ግን አንዳንድ የሕግ አውጪዎች ሃሳቡ ለፖለቲካዊ ሳንሱር አደገኛ ምሳሌ ሊሆን እንደሚችል እና ከቴክኒክ እና ሕግ አንጻር ለትግበራ አስቸጋሪ እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል፡፡
ℹ ይህ ዜና ምዕራቡ ዓለም በሩሲያ ሚዲያዎች ላይ ለዓመታት እየጨመረ የመጣ ጫና እያሳደረ ባለበት ወቅት የመጣ ሲሆን ሞስኮ የምርጫ ጣልቃ ገብነት ክሶች እና ማዕቀቦችን መሠረተ ቢስ እና አድሎዓዊ ስትል ትገልጻቸዋለች፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X