አፍሪካና ሩሲያ የዩራኒየም ማዕድን ማውጣትን ጨምሮ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ በጋራ ይሠራሉ - የሩሲያ ኢነርጂ ሚኒስቴር
15:29 30.10.2025 (የተሻሻለ: 15:34 30.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አፍሪካና ሩሲያ የዩራኒየም ማዕድን ማውጣትን ጨምሮ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ በጋራ ይሠራሉ - የሩሲያ ኢነርጂ ሚኒስቴር
ሩሲያ ከኢነርጂ ዘርፍ ውጪ ወርቅ እና ሌሎች ማዕድናት ማውጣትን ጨምሮ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የጋራ ፕሮጀክቶች አሏት ሲሉ የሩሲያ ምክትል ኢነርጂ ሚኒስትር ሮማን ማርሻቪን ተናግረዋል፡፡
በርካታ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን የማዘጋጀት ሂደት በመንግሥታት ኮሚሽኖች በኩል እየተጀመሩ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ማርሻቪን ሐሙስ ዕለት በእቴጌ ካትሪን ሴንት ፒተርስበርግ የማዕድን ዩኒቨርሲቲ 'የልማት መንገድ፤ ጥሬ ዕቃዎችና የሰው ኃይል የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት መሠረት' በሚል ርዕስ በተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ የጥሬ ዕቃዎች ውይይት ላይ ተሳትፈዋል፡፡
የማዕድን ዩኒቨርሲቲው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ማራት ሩዳኮቭ እንደተናገሩት፤ ዩኒቨርሲቲው በማዕድን ሀብት አጠቃቀም መስክ ለሩሲያ-አፍሪካ ትብብር መደበኛ የውይይት መድረክ ለማቋቋም አቅዷል፡፡
ውጥኑ የጋራ ሳይንሳዊ ቡድኖችን መፍጠር፣ ለአፍሪካ ሀገራት የሰው ኃይል ሥልጠና እና ከሥነ-ምድራዊ አሰሳ ጋር የተያያዙ የጋራ ፕሮጀክቶችን ያካትታል ብለዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X