በእንስሳት ሃብት እና የእንስሳት ተዋጽዖ ምርቶች ላይ ያተኮረ ዐውደ ርዕይ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበእንስሳት ሃብት እና የእንስሳት ተዋጽዖ ምርቶች ላይ ያተኮረ ዐውደ ርዕይ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
በእንስሳት ሃብት እና የእንስሳት ተዋጽዖ ምርቶች ላይ ያተኮረ ዐውደ ርዕይ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.10.2025
ሰብስክራይብ

በእንስሳት ሃብት እና የእንስሳት ተዋጽዖ ምርቶች ላይ ያተኮረ ዐውደ ርዕይ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

ከጥቅምት 20-22፣ 2018 ዓ.ም ድረስ በሚቆየው ዓመታዊ የዶሮ፣ የዓሣ እርባታ እና የንብ ማነብ ኤግዚቢሽን፤ በእንስሳት ሃብት እና እሴት ሰንሰለት ላይ የተሠማሩ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የዘርፉ ተዋናዮች፣ አምራቾች፣ አቅራቢዎችና ባለሙያዎች ይሳተፉበታል ተብሏል።

በዐውደ ርዕዩ መክፈቻ ላይ የተገኙት በግብርና ሚኒስቴር የእንሰሳት እና ዓሣ ሀብት ሚኒስትር ዴዔታ ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር አለማየሁ መኮንን፤ ኢትዮጵያ ያልተነካ እምቅ የእንሰሳት ሀብት ቢኖራትም ከዘርፉ የሚጠበቀውን ያህል አልተጠቀመችም ብለዋል።

ኤክስፖው እምቅ ሀብቱን ለማስተዋወቅና የገበያ ዕድሎችን ለመፍጠር እንደሚጠቅም ጨምረው ገልፀዋል።

ከ14 ሀገራት የተወጣጡ ከ100 በላይ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ እና የመኖ ግብዓት አቅራቢዎች እንዲሁም ሀገር በቀል ኩባንያዎች በዐውደ ርዕዩ እንደሚሳተፉ የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በእንስሳት ሃብት እና የእንስሳት ተዋጽዖ ምርቶች ላይ ያተኮረ ዐውደ ርዕይ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ - Sputnik አፍሪካ
1/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በእንስሳት ሃብት እና የእንስሳት ተዋጽዖ ምርቶች ላይ ያተኮረ ዐውደ ርዕይ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ - Sputnik አፍሪካ
2/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በእንስሳት ሃብት እና የእንስሳት ተዋጽዖ ምርቶች ላይ ያተኮረ ዐውደ ርዕይ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ - Sputnik አፍሪካ
3/3
1/3
2/3
3/3
አዳዲስ ዜናዎች
0