የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የባቡር ክፍሎች እና መለዋወጫዎች ማምረቻ ማዕከል ሊያቋቁም ነው
13:32 30.10.2025 (የተሻሻለ: 13:34 30.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የባቡር ክፍሎች እና መለዋወጫዎች ማምረቻ ማዕከል ሊያቋቁም ነው
ለዚህም ድርጅቱ ከደቡብ አፍሪካው ፊዛ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር ስምምነት ተፈራርሟል።
መግባቢያው በሀገሪቱ ያለውን የባቡር መለዋወጫ እጥረት በመቅረፍ፣ የውጭ ምንዛሬ በማስቀረት እና ገበያውን በማጠናከር፤ ምርቶችን ለአፍሪካ ሀገራት ለማቅረብ ያስችላል ሲል ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል፡፡
የስምምነቱ ማዕቀፎች፦
በባቡር ጉዳዮች ላይ የቴክኒክ ድጋፍ ማግኘት፣
ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማትና ኢንቨስተሮች ጋር ትስስር መፍጠር፣
የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች መስጠት እና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ በትብብር መሥራት።
ፊዛ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በደቡብ አፍሪካ፣ ህንድ፣ በመካከለኛው ምስራቅና በአሜሪካ የባቡር አካላት እና መለዋወጫ እንደሚያቀርብ ተመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X