የስፑትኒክ ፕሮ የሚዲያ ትምህርታዊ ጉባኤ በኢትዮጵያ ተካሄደ

© Photo Media Center of Excellence (EMCoE) of the Ethiopian Media AuthoritySputnikPro Ethiopia
SputnikPro Ethiopia - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.10.2025
ሰብስክራይብ
‘ስፑትኒክፕሮ’ በዓለም አቀፉ የዜና ኤጀንሲ ስፑትኒክ የተጀመረ ዓለም አቀፍ የሚዲያ ትምህርት ፕሮጀክት ነው። በሩሲያ እና በውጭ ሀገር ከፍተኛ የመገናኛ ብዙኃን ሥራ አስኪያጆች፣ ባለሙያዎች እና ግንባር ቀደም የኤጀንሲው ባለሙያዎች ለጋዜጠኞች፣ ለፕሬስ ኦፊሰሮች፣ ለጦማሪዎች እና ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ልዩ ሴሚናሮች፣ ንግግሮች እና የማስተርስ ትምህርቶች የሚሰጡበት ልዩ ፕሮግራም ነው።
የስፑትኒክ ፕሮ ተናጋሪዎች በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የመገናኛ ብዙኃን የልህቀት ማዕከል የትምህርት ፕሮግራም ሥር ለጋዜጠኞች፣ ለተማሪዎች እና ለአካዳሚክ ባለሙያዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡
የስፑትኒክ ዓለም አቀፍ ትብብር ዳይሬክተር ቫሲሊ ፑሽኮቭ፤ ስለ ሩሲያ የመገናኛ ብዙኃን ምህዳር ዝርዝር ጉዳዮች እና በዘመናዊ ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ውስጥ ስላሉ ዋና ዋና አዝማሚያዎች ለታዳሚዎች ንግግር አድርገዋል፡፡ በጆሃንስበርግ የስፑትኒክ ቢሮ ኃላፊ ቪክቶር አኖኪን፤ በመገናኛ ብዙኃን ውስጥ ስላሉ የሐሰት ዜናዎች ሀሳቦችን አጋርተዋል።
ከ50 በላይ ተሳታፊዎች በዌቢናሩ ላይ በመገኘት ስለ ሩሲያ የመገናኛ ብዙኃን አወቃቀር፣ የዜጎች ጋዜጠኝነት እድገት፣ በደቡባዊ ዓለም የመገናኛ ብዙኃን ትብብር እና የሐሰት ዜናዎች መከላከያ ዘዴዎችን በተመለከት ጥያቄዎችን አቅርበዋል።
© Photo Media Center of Excellence (EMCoE) of the Ethiopian Media Authorityየስፑትኒክ ፕሮ የሚዲያ ትምህርታዊ ጉባኤ በኢትዮጵያ ተካሄደ
የስፑትኒክ ፕሮ የሚዲያ ትምህርታዊ ጉባኤ በኢትዮጵያ ተካሄደ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.10.2025
የስፑትኒክ ፕሮ የሚዲያ ትምህርታዊ ጉባኤ በኢትዮጵያ ተካሄደ

"በበየነ መረብ ውይይቶች ላይ ሀገራዊ ልምዶቻቸውን እና የዘርፉ ተጨባጭ ማሳያዎችን በማጋራት የመወያያ ርዕሶችን ስለሚያዳብሩ፤ የዓለም አቀፍ እንግዶች ተሳትፎ ለፕሮግራሞቻችን ወሳኝ ናቸው" ሲሉ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የመገናኛ ብዙኃን የልህቀት ማዕከል አማካሪ አቶ አንተነህ ፀጋዬ ተናግረዋል፡፡

የፕሮግራሙ አዘጋጆች የስፑትኒክ ንግግር አድራጊዎችን ከፍተኛ የእውቀት ደረጃ እና ሙያዊ ብቃት አፅንዖት ሰጥተው፤ በመገናኛ ብዙኃን ማዕከሉ የትምህርት ፕሮጀክቶች ዙሪያ ቀጣይ ትብብሮች እንደሚኖሩ ተስፋቸውን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ፤ የመገናኛ ብዙኃን ሙያዊ ብቃት ደረጃን በላቀ ሁኔታ ለማዳበር እና የሀገሪቱን የመገናኛ ብዙኃን ገጽታ የማሳደግ ግቦችን ያነገበ ብሔራዊ የመገናኛ ብዙኃን የልህቀት ማዕከሏን በቅርቡ አስመርቃለች። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የጋዜጠኞችን አቅም በተለያዩ መንገዶች ለመገንባት የሚያስችል ዘመናዊ ማዕከል ለማቋቋም ይህንን ብሔራዊ ተነሳሽነት ወስዷል። ባለሥልጣኑ የኢትዮጵያን የመገናኛ ብዙኃን ምህዳር የሚቆጣጠር፣ የሚከታተል እና የሚመራ ገለልተኛ የሕዝብ ተቋም ነው።
አዳዲስ ዜናዎች
0