እስራኤል ትናንት ምሽት በጋዛ ከፈፀመቻቸው ጥቃቶች በኋላ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ቀጥላለች - የሀገሪቱ ጦር

ሰብስክራይብ

እስራኤል ትናንት ምሽት በጋዛ ከፈፀመቻቸው ጥቃቶች በኋላ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ቀጥላለች - የሀገሪቱ ጦር

"በደርዘን የሚቆጠሩ የሽብር ኢላማዎች እና አሸባሪዎች" ላይ ጥቃት ካደረሰ በኋላ በፖለቲካ አመራሮች ትዕዛዝ መሠረት፤ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ማስፈጸም እንደቀጠለ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል። ነገር ግን "ለማንኛውንም ጥሰት ጥብቅ ምላሽ ይሰጣል" ብሏል።

▪የኔታንያሁ ጽህፈት ቤት ሃማስ በጋዛ ውስጥ አሁንም ተይዘው የሚገኙትን ከመመለስ ይልቅ እስራኤል አስቀድማ ያገኘችውን የታጋቾች አስከሬን በመመለስ የጋዛ ተኩስ አቁም ስምምነትን ጥሷል ሲል ማክሰኞ ዕለት ከሷል።

የጋዛ ጤና ሚኒስቴር በእስራኤል ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች እንደተገደሉ እና ከ250 በላይ መቁሰላቸውን ገልጿል።

የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥቃቶቹን "ግልጽ የተኩስ አቁም ጥሰት" ሲል የጠራ ሲሆን እስራኤል ስምምነቱን "ሙሉ በሙሉ እንድታከብር" እና "ሰላምንና መረጋጋትን ከሚያናጉ ድርጊቶች እንድትቆጠብ" አሳስቧል።

ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘው ተንቀሳቃሽ ምሥል የእስራኤል ጥቃት ያስከተለውን ውድመት ያሳያል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0