ሩሲያ እንደ ፖሳይዶን ያሉ ሰርጓጅ የኒውክሌር ድሮኖችን ከዓለም አቀፍ ሕጎች ጋር በሚጣጣም መልኩ ነው የምትሞክረው - የክሬምሊን ቃል አቀባይ
19:00 29.10.2025 (የተሻሻለ: 19:04 29.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ እንደ ፖሳይዶን ያሉ ሰርጓጅ የኒውክሌር ድሮኖችን ከዓለም አቀፍ ሕጎች ጋር በሚጣጣም መልኩ ነው የምትሞክረው - የክሬምሊን ቃል አቀባይ
በዲሚትሪ ፔስኮቭ የተሰጡ ዋና ዋና መግለጫዎች፦
◻ የፖሳይዶን ሙከራ ለሩሲያ ደህንነት እንዲሁም በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ጥቅም ላይ ሊውሉ ለሚችሉ ቴክኖሎጂዎች አዲስ እርምጃ ነው፡፡
◻ ፑቲን የፖሳይዳን ሙከራዎችን በግል ባይመለከቱም ገለጻ ተደርጎላቸው፤ ሁሉንም መረጃዎች በቅርበት ተከታትለዋል፡፡
◻ ከአውሮፓ የሚወጡ መግለጫዎች የኦሬሽኒክ ሚሳኤል ስርዓት ለሩሲያ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ግልጽ አድርጓል፡፡
◻ አውሮፓ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሩሲያ ጠል አስተሳሰቧን ትተዋለች ብሎ ማሰብ አይቻልም፡፡
◻ ሩሲያ በዩሬዥያ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሀገራት ተቀራራቢነት አለመረሳቱን የማረጋገጥ ፍላጎት አላት፡፡
◻ ሞስኮ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ፍላጎቷ ላይ በመመስረት መደራደር ትፈልጋለች፡፡
◻ በቬንዙዌላ አቅራቢያ የአሜሪካ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከዓለም አቀፍ ሕግ ጋር በሚጣጣም መልኩ መከናወን አለበት፡፡
◻ በቬንዙዌላ ዙሪያ ያለው ሁኔታ ሩሲያ ከዋሽንግተን ጋር በምታደርገው የሁለትዮሽ ግንኙነት አጀንዳ አይደለም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X