የውጭ የስለላ ኤጀንሲዎች የሱዳን ወታደሮችን የቴሌኮም ግንኙነት በማቋረጥ የኤል-ፋሸርን መያዝ አቀናብረዋል - የዳርፉር አስተዳዳሪ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየውጭ የስለላ ኤጀንሲዎች የሱዳን ወታደሮችን የቴሌኮም ግንኙነት በማቋረጥ የኤል-ፋሸርን መያዝ አቀናብረዋል - የዳርፉር አስተዳዳሪ
የውጭ የስለላ ኤጀንሲዎች የሱዳን ወታደሮችን የቴሌኮም ግንኙነት በማቋረጥ የኤል-ፋሸርን መያዝ አቀናብረዋል - የዳርፉር አስተዳዳሪ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.10.2025
ሰብስክራይብ

የውጭ የስለላ ኤጀንሲዎች የሱዳን ወታደሮችን የቴሌኮም ግንኙነት በማቋረጥ የኤል-ፋሸርን መያዝ አቀናብረዋል - የዳርፉር አስተዳዳሪ

ሚኒ አርኮ ሚናዊ በቴሌቪዥን ባስተላለፉት ንግግር፤ ከግንቦት 2024 ጀምሮ በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ከበባ ስር የነበረችው ከተማ፤ “ጠብ ጫሪ መንግሥታት” ለአማጺው ቡድን ቁሳዊ፣ የሎጅስቲክ እና የስለላ ድጋፍ ባይሰጡ ኖሮ ከቁጥጥራችን ውጪ አትሆንም ነበር ብለዋል።

ሚናዊ፤ በተለይ የስለላ ኤጀንሲዎች “ሁሉንም ዘመናዊ የሳተላይት ግንኙነቶች በማቋረጥ”፤ በመንግሥት የምድር ጦር ኃይሎች፣ በተባባሪ ቡድኖች እና በማዘዣ ጣቢያዎች መካከል ያለውን ግንኙነት እንደበጣጠሱ ጠቅሰዋል።

🪖 የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ “ከጎረቤት ሀገራት እና ከውጭ ቅጥረኞች፤ ብሎም ከግንኙነት ማወኪያ ቴክኖሎጂ ጋር ተጣምረው ከውጭ በሚዘወሩ ድሮኖች” እንደሚመካ ገልፀዋል።

ሚናዊ በእርሳቸው አመራር ሥር የነበሩ ድክመቶችን ተቀብለው፤ የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ “አሳፋሪ ዝምታ” በፅኑ የተቹ ሲሆን የዓለም ኃያላን “ሰብዓዊነትን በመተው” እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ “የፋይናንስ ድጋፍ ሰጪዎች” “ገንዘብን ለዘር ማጥፋት እንዲያውሉ” ፈቅደዋል ሲሉ ወንጅለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0