ኢትዮጵያ በፋብሪካ የታገዘ የተገጣጣሚ ቤት ግንባታን ልታስጀምር ነው
18:14 29.10.2025 (የተሻሻለ: 18:24 29.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በፋብሪካ የታገዘ የተገጣጣሚ ቤት ግንባታን ልታስጀምር ነው
በሀገሪቱ ያለውን የቤት ልማት ዘርፍ ለማሳደግ ፋብሪካዎች በቀጣይ ወራት ወደ ሥራ እንደሚገቡ እና የቤቶች ግንባታ እንደሚጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል፡፡
ባለ ሶስት ወለል የሆኑ ከ4-5 ማሳያ ቤቶችን በፋብሪካ በሚመረቱ ግብዓቶች በመገጣጠም አዲስ አበባ ላይ በቀጣይ አንድ ወር ውስጥ ገንብቶ ለማጠናቀቅ መታቀዱን ጠቁመዋል፡፡
በዘርፉ ያለውን ችግር ለመቅረፍ በራስ አቅም የብረት፣ የሲሚንቶ፣ የመስታወት እና መሠል የግንባታ ግብዓቶች ምርት ለማሳደግ መንግሥት በቁርጥኝነት እየሠራ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡
በቀጣይ 6 ዓመታት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ቤቶችን ለመሥራት ግብ ተቀምጧል፡፡ ፕሮጀክቱ 3 ትሪሊዮን ብር ኢንቨስትመንት ሊጠይቅ እንደሚችል ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከሀገሪቱ ዓመታዊ በጀት 20 በመቶውን እንደሚይዝም ገልፀዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X