ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ሰላም እና መረጋጋት በድጋሚ ቁርጠኝነቷን አረጋገጠች
16:20 29.10.2025 (የተሻሻለ: 17:04 29.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ሰላም እና መረጋጋት በድጋሚ ቁርጠኝነቷን አረጋገጠች
የቀጣናውን የኢኮኖሚ ውህደት ለማሻሻል የመሠረተ ልማት ትስስርን ማጠናከር ወሳኝ እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ፤ የደቡበ ሱዳን አቢዬ ኮሚቴ ከፍተኛ ልዑክን በአዲስ አበባ አግኝተው ባነጋገሩበት ወቅት አስረግጠዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር አኩዬ ቦና ማልዋልን የሚያካትተው የልዑካን ቡድን፤ በደቡብ ሱዳን በተለይም በአቢዬ ስላለው ወቃትዊ ሁኔታ ለሚኒስትር ጌዲዮን ገለጻ አድርጓል፡፡
ልዑኩ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በተሳካ ሁኔታ መመረቁን አስመልክቶም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት እንዳስተላለፈ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X