የሩሲያ ጦር በዩክሬን ወታደራዊ ዘመቻ በሁሉም ግንባር እየገሰገሰ ነው - ፑቲን

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ ጦር በዩክሬን ወታደራዊ ዘመቻ በሁሉም ግንባር እየገሰገሰ ነው - ፑቲን
የሩሲያ ጦር በዩክሬን ወታደራዊ ዘመቻ በሁሉም ግንባር እየገሰገሰ ነው - ፑቲን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.10.2025
ሰብስክራይብ

የሩሲያ ጦር በዩክሬን ወታደራዊ ዘመቻ በሁሉም ግንባር እየገሰገሰ ነው - ፑቲን

ቭላድሚር ፑቲን ይህን የተናገሩት በዛሬው እለት በማዕከላዊ ወታደራዊ ሆስፒታል ህክምና ላይ ከሚገኙ ወታደራዊ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት ነው።

ፕሬዝዳንቱ በሠራዊት ግስጋሴ፣ በቡሬቬስትኒክ ሚሳኤል፣ በፖሰይደን የኒውክሌር ድሮን ዙሪያ ያደረጉት ንግግር ዋና ዋና ነጥቦች፦

ዩክሬን

◻ በወታደራዊ ዘመቻው ቀጣና ውስጥ ሁኔታው ለሩሲያ በጥሩ ሁኔታ እየተሻሻለ ነው።

◻ ሩሲያ በአሁኑ ወቅት የረጅም ጊዜ ደህንነቷን በግምባር ላይ እያረጋገጠች ነው።

◻ የዩክሬን ኃይሎች በኩፒያንስክ እና ክራስኖአርሜይስክ ውስጥ ታግተው እና ተከበዋል ይገኛሉ።

◻ የሩሲያ ኃይሎች የዩክሬን ወታደሮች በተከበቡባቸው ዞኖች ውስጥ የውጭ ጋዜጠኞች ቅኝት በሚያደርጉበት ወቅት ውጊያውን ለማቆም ቁርጠኛ ናቸው።

ቡሬቬስትኒክ ሚሳኤል

አዲሱ የሩሲያ ቡሬቬስትኒክ ሚሳኤል "የማይካዱ ጥቅሞች" አሉት።

የሚሳኤሉ ተርቦጄት ሬአክተር ከኒውክሌር ሰርጓጅ መርከብ በአንድ ሺህ እጥፍ ያነሰ ቢሆንም የኃይል ማመንጫቸው ተመጣጣኝ ነው።

በቡሬቬስትኒክ ውስጥ የተገጠመው የኒውክሌር ሬአክተር "በደቂቃዎች እና በሰከንዶች ውስጥ" ይነሳል።

ሩሲያ በምርምር ባለሙያዎቿ ባስመዘገበችው እድገት ኩራት ሊሰማት ይገባል።

ፖሳይደን የኒውክሌር የውሃ ውስጥ ድሮን

ሩሲያ የፖሳይደን የውሃ ውስጥ ድሮኗን በተሳካ ሁኔታ ሞክራለች።

መሳሪያው የኒውክሌር ተርቦጄት ሞተር የተገጠመለት ነው።

በአሁኑ ጊዜ ዓለም ላይ "የሚመጣጠነው ምንም ነገር የለም"፤ በቅርብ ጊዜ ውስጥም ሊኖር አይችልም።

መሳሪያውን ማጨናገፍ "የማይቻል" ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0