ፑቲን ለልደታቸው ከወታደሮች ለተበረከቱላቸው በጥይት የተመቱ የቅዱሳን አዶ ስጦታዎች ምሥጋና አቀረቡ

ሰብስክራይብ

ፑቲን ለልደታቸው ከወታደሮች ለተበረከቱላቸው በጥይት የተመቱ የቅዱሳን አዶ ስጦታዎች ምሥጋና አቀረቡ

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሞስኮን ማዕከላዊ ወታደራዊ ክሊኒካል ሆስፒታል በጎበኙበት ወቅት፤ በውጊያ ከደረሰባቸው ጉዳት እያገገሙ ከሚገኙ የሩሲያ ወታደሮች ለተሰጣቸው በጥይት የተበሱ የቅዱሳን ስዕላት ጥልቅ ምሳሌያዊ የልደት ስጦታ አመሥግነዋል፡፡

“በጦርነት ራሳችሁን እየሰዋችሁ፤ ህይወታችሁን እና ጤናችሁን አደጋ ላይ ጥላችሁ፤ የልደቴን ቀን በማስታወስ ስጦታ ብቻ ሳይሆን፤ ህይወታችሁን የጠበቁ የቅዱሳን መታሰቢያ ልካችኋል። እነዚህ የጥይት ምልክቶች እነዚህ አዶዎች እንዴት እንደጠበቋችሁ ያሳያሉ” ሲሉ ፑቲን ለወታደሮቹ ተናግረዋል፡፡

ስጦታው እጅግ ስሜታቸውን እንደነካው እና ወዲያውኑ ወታደሮቹን በአካል እንዲያገኙ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል፡፡

“በቅድሚያ እና ከሁሉም በላይ ለእናት ሀገር ላደረጋችሁት አገልግሎት ማመስገን እፈልጋለሁ” ብለዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0