ፕሬዝዳንት ፑቲን ቡሬቬስትኒክ ሚሳኤልን በተመለከተ የሰጧቸው ቁልፍ መግለጫዎች፦
15:23 29.10.2025 (የተሻሻለ: 15:24 29.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፕሬዝዳንት ፑቲን ቡሬቬስትኒክ ሚሳኤልን በተመለከተ የሰጧቸው ቁልፍ መግለጫዎች፦
▪ የ "ቡሬቬስትኒክ" ሚሳኤል የሩሲያን የመከላከያ አቅም ከማሳደግ ባለፈ ለሳይንስም ትልቅ ግኝት ነው፡፡
▪ "ቡሬቬስትኒክ" የማያሻማ የበላይነትን ይሰጣል፤ ሩሲያ በሳይንቲስቶቿ እና በልዩ ባለሙያዎቿ ስኬቶች ልትኮራ ይገባል፡፡
▪ የ "ቡሬቬስትኒክ" ጥቅም የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ክፍሉ ላይ የተመሰረት ሲሆን ከኒውክሌር ሰርጓጅ መርከብ ሬአክተር በሺህ እጥፍ ቢያንስም ኃይሉ ግን ተመጣጣኝ ነው፡፡
▪ በ "ቡሬቬስትኒክ" ውስጥ የተገጠመው የኒውክሌር ሬአክተር “በደቂቃዎች እና በሰከንዶች ውስጥ” ሥራ ይጀምራል፡፡
▪ በ "ቡሬቬስትኒክ" ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉት ኤሌክትሮኒኮች ከወዲሁ በህዋ ፕሮግራሞች ውስጥ መተግበር ጀምረዋል፡፡
▪ ሩሲያ ለ "ቡሬቬስትኒክ" ጥቅም ላይ የዋሉ የኒውክሌር ቴክኖሎጂዎችን በሲቪል ኢኮኖሚ ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ትችላለች፡፡
▪ እነዚህ የኒውክሌር ቴክኖሎጂዎች በጨረቃ ፕሮግራም ውስጥም ጥቅም ላይ ይውላሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X