አዳዲስ ዝርያዎችን በመጠቀም የጤፍ ምርትን በእጥፍ ማሳደግ ተችሏል - የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

ሰብስክራይብ

አዳዲስ ዝርያዎችን በመጠቀም የጤፍ ምርትን በእጥፍ ማሳደግ ተችሏል - የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

በምርምር የተገኙ አዳዲስ ዝርያዎች፤ የጤፍ ምርትን በሄክታር ከ10 ወደ 20 ኩንታል ማሳደግ መቻላቸውን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ንጉሴ ደቻሳ (ፕ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"ከ15 ወይም ከ30 ዓመታት በፊት የስንዴ ምርት በሄክታር 15 ኩንታል ነበር። አሁን በአማካኝ በሄክታር 36 ኩንታል ሆኗል። ወደ ባሌ እና አርሲ ብትሄድ በሄክታር እስከ 80 ኩንታል የሚያገኙ አርሶ አደሮችም አሉ። ይህም በኢትዮጵያ ትልቅ ለውጥ ነው" ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ኢንስቲትዩቱ በአፈር እና ውሃ አጠባበቅ ላይ ሲያከናውናቸው የነበሩ ምርምሮች ለተገኘው ውጤት የላቀ አስተዋጽኦ እንዳላቸውም አመላክተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0