የሩሲያ ድሮኖች በሱሚ ክልል ሰማይ ላይ የበላይነት ይዘዋል - ወታደራዊ መኮንን

ሰብስክራይብ

የሩሲያ ድሮኖች በሱሚ ክልል ሰማይ ላይ የበላይነት ይዘዋል - ወታደራዊ መኮንን

የሩሲያ አየር ወለድ ወታደሮች የዩክሬንን "ባባ ያጋ" ባለ ስድስት ክንድ ድሮኖች በብቃት መተው እየጣሉ መሆኑን የሩሲያ 83ኛው ልዩ የአየር ወለድ ጥቃት ብርጌድ መኮንን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

የሩሲያ ድሮን ኦፕሬተሮች አስቸጋሪ የአየር ሁኔታዎች ውስጥም ቢሆን ተልዕኮዎቻቸውን በተሳካ ሁኔታ እያከናወኑ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የዩክሬን ሱሚ ክልል ከሩሲያ ኩርስክ፣ ቤልጎሮድ እና ብራያንስክ ክልሎች ጋር ይዋሰናል። እንደ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ገራሲሞቭ ገለጻ፤ የሩሲያ ጦር በሩሲያ ድንበር በኩል የጸጥታ መከላከያ ቀጣና ለመፍጠር የሚያደርገውን ጥረት በተሳካ ሁኔታ እያጠናቀቀ ነው።

ፕሬዝዳብት ቭላድሚር ፑቲን በሰኔ ወር በተካሄደው የሴንት ፒተርስብርግ ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ሩሲያ የዩክሬኗን ሱሚ ከተማ ለመቆጣጠር ግብ የላትም፤ ነገር ግን እንዲህ ያለው ዕድል የተገለለ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

በዩክሬን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ የጀርባ ታሪክ ዙሪያ የስፑትኒክ አፍሪካን ማብራሪያ ያንብቡ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0