ኢትዮጵያ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 13 ሺህ 443 የሳይበር ጥቃቶች እና የጥቃት ሙከራዎች ማስተናገዷ ተገለፀ
19:12 28.10.2025 (የተሻሻለ: 19:14 28.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 13 ሺህ 443 የሳይበር ጥቃቶች እና የጥቃት ሙከራዎች ማስተናገዷ ተገለፀ
ባለፉት ሶስት ወራት ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችሉ ከነበሩ 896 የሳይበር ጥቃቶች መካከል 874 ያህሉን መከላከል መቻሉን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሐሚድ አስታውቀዋል። ቀሪዎቹ 22 ጥቃቶች በትንተና ሂደት ላይ ናቸው።
በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣው የሳይበር ጥቃት እና ሙከራ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በእጅጉ ጨምሯል፡፡
የአስተዳደሩ የሳይበር ጥቃቶችን የመከላከል አቅም በ2018 የመጀመሪው ሩብ ዓመት 97.8 በመቶ መድረሱን ኃላፊዋ አያይዘው ጠቁመዋል፡፡
የተቋሙን የሩብ ዓመት አፈፃፀም የገመገመው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የሳይበር ጥቃቶችን የመከላከል አቅም ከ99 በመቶ በላይ ማሳደግ እንደሚገባ አሳስቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X