የሩሲያ-አሜሪካ የመሪዎች ስብሰባ ከተካሄደ፤ በእርግጠኝነት በቡዳፔስት ይሆናል - የሃንጋሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ-አሜሪካ የመሪዎች ስብሰባ ከተካሄደ፤ በእርግጠኝነት በቡዳፔስት ይሆናል - የሃንጋሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
የሩሲያ-አሜሪካ የመሪዎች ስብሰባ ከተካሄደ፤ በእርግጠኝነት በቡዳፔስት ይሆናል - የሃንጋሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.10.2025
ሰብስክራይብ

የሩሲያ-አሜሪካ የመሪዎች ስብሰባ ከተካሄደ፤ በእርግጠኝነት በቡዳፔስት ይሆናል - የሃንጋሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ፔተር ሲያርቶ ይህን ያረጋገጡት ከሰርጌ ላቭሮቭ ጋር በሚንስክ ከተነጋገሩ በኋላ በማህበራዊ ሚዲያ ባሠራጩት ተንቀሳቃሽ ምሥል ነው።

በተጨማሪም ሩሲያ ለሃንጋሪ የኃይል አቅርቦት ለማስቀጠል ዝግጁ መሆኗን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን በሚቀጥለው ሳምንት ወደ አሜሪካ በሚያደርጉት ጉብኝት ይህንን መወያየት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም ኦርባን በሩሲያ ዘይት ላይ የተጣሉትን ማዕቀቦች ከትራምፕ ጋር ለመወያየት ማቀዳቸውን ገልጸው፤ የኃይል አቅርቦቱ ከሩሲያ የሚመጣ ካልሆነ በሃንጋሪ የዋጋ ንረት እንደሚባባስ ተከራክረዋል።

ሲያርቶ እና ላቭሮቭ በዩክሬን ዙሪያ ባደረጉት ውይይት፤ ኪዬቭ የቋንቋ እና የሐይማኖቶችን ጨምሮ የህዳጣን ማኅበረሰብ መብቶችን ስርዓታዊ በሆነ መንገድ እንደምትጥስ አጽንኦት ሰጥተዋል ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከውይይታቸው በኋላ ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0