አፍሪካ የተፈጥሮ ሐብቷን ከቴክኖሎጂ ጋር ይበልጥ ማስተባበር አለባት

ሰብስክራይብ

አፍሪካ የተፈጥሮ ሐብቷን ከቴክኖሎጂ ጋር ይበልጥ ማስተባበር አለባት

አኅጉሪቱ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዕምቅ የተፈጥሮ ሐብቷን በውጤታማነት መጠቀም የሚያስችል የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስልት ማስፋት እንዳለባት የደቡብ አፍሪካ ሀገራት የባዮሳይንስ አውታረ መረብ ማናጀር ኤሬክ ቻካውያ (ፕ/ር) ገልፀዋል።

"አፍሪካ ሁሉም ለማለት በሚያስደፍር ደረጃ የግብርና ግብዓቶች አሏት። ምርት ላይ እሴት መጨመር የሚችሉ ብሩህ አዕምሮ ያላቸው ወጣቶችም እንዲሁ። አቅሞችን የሚያስተሳስር ሥርዓት መፍጠር ቁልፍ ጉዳይ ነው" ብለዋል።

ፕሮፌሰሩ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ሩሲያ፣ ቻይና እና ሕንድ ከራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተስማሙ ስልተ ምርቶችን በመንደፍ ረገድ ያስመዘገቡትን እመርታም አንስተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0