ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በቀይ ባህር ዙርያ ከኤርትራ ጋር እንዲያደራድር ጥሪ አቀረበች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በቀይ ባህር ዙርያ ከኤርትራ ጋር እንዲያደራድር ጥሪ አቀረበች
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በቀይ ባህር ዙርያ ከኤርትራ ጋር እንዲያደራድር ጥሪ አቀረበች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.10.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በቀይ ባህር ዙርያ ከኤርትራ ጋር እንዲያደራድር ጥሪ አቀረበች

“የኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ተጠቃሚነት ጉዳይ አይቀሬ ስለሆነ፤ ቅድሚያ የምንሰጠውም ሰላምና ንግግር ስለሆነ ሸምግሉንና መፍትሄ አምጡለን፤ ይሄ ነው ጥያቄያችን” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ ከአሜሪካ፣ ከሩሲያ፣ ከቻይና፣ ከአፍሪካ ኅብረት እና ከአውሮፓ ኅብረት ጋር ውይይት ማድረጋቸውን አንስተዋል።

በፍፁም የውጊያ መሻት የለንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ በሕጋዊ እና በንግግር ሰላማዊ መፍትሄ ሊገኝ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

“በአንድ ቀን አላጣነውም በአንድ ቀን አንመልሰውም ተፈጥሯዊ ሂደቱን ጠበቆ ይሄዳል" ሲሉ የባሕር በር የማግኘት ውጥኑ አይቀሬ መሆኑን አስረግጠው አስረድተዋል፡፡

የኤርትራን ነጻነት ተከትሎ ኢትዮጵያ የባሕር በር አልባ ከሆነች 34 ዓመት በኋላ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዳግም ውጥረት ውስጥ ገብቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0