የአፍሪካ ቻይና ትብብር በአዲስ የደቡብ-ደቡብ የትብብር ምዕራፍ ላይ እንደምንገኝ የሚያሳይ ነው - የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት
17:13 28.10.2025 (የተሻሻለ: 17:24 28.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ቻይና ትብብር በአዲስ የደቡብ-ደቡብ የትብብር ምዕራፍ ላይ እንደምንገኝ የሚያሳይ ነው - የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት
አዲስ የተመሠረተው የአፍሪካ ቻይና የግብርና ሳይንስ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ትብብር፤ በአፍሪካ እና ቻይና መካከል ያለውን ጠንካራ ህብረት የሚያሳይ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕ/ር ንጉሴ ደቻሳ ተናግረዋል።
ኃላፊው ይህንን ያሉት ትኩረቱን በግብርና ምርምር እና ፈጠራ ላይ ያደረገ ኤግዚቢሽን በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ዛሬ ሲከፈት ነው።
ፕ/ር ንጉሴ ደቻሳ "የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ባለፉት 60 ዓመታት ከጥናትና ምርምር ባለፈ ለውጭ ምንዛሬ ግኝት ጭምር የጠቀሙ አበረታች ሥራዎችን ሠርቷል" ሲሉ በኤግዚቢሽኑን መክፈቻ ተናግረዋል።
ለቀጣዮቹ ሁለት ቀናት በሚዘልቀው ኤግዚቢሽን በምርምር ተቋሙና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ ማዕከላቱ የተገኙ አዳዲስ የምርምር ውጤቶችና የግብርና ቴክኖሎጂዎች ለእይታ እንደሚቀርቡ ተገልጿል። ትናንት በአዲስ አበባ በተካሄደ ጉባኤ የአፍሪካ ቻይና የግብርና፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ትብብር መመሥረቱ የሚታወስ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X


