የቻይና-አፍሪካ የግብርና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ጥምረት ስድስት የግብርና ፈጠራ ፕሮጀክቶችን ይፋ አደረገ
16:06 28.10.2025 (የተሻሻለ: 16:14 28.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የቻይና-አፍሪካ የግብርና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ጥምረት ስድስት የግብርና ፈጠራ ፕሮጀክቶችን ይፋ አደረገ
በልማት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሥልጠና እና የቴክኒክ ድጋፍ ላይ ካተኮሩት ስድስት ፕሮጀክቶቹ ውስጥ አራት ንዑስ ፕሮጀክቶች ለኢትዮጵያ ተመድበዋል፡፡
“ኢትዮጵያ ከቻይና ሰፊ የቴክኖሎጂ ልምድ በመቅሰም በጥራትም ሆነ በብዛት ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥታለች፤ የእነሱን እውቀት ከሀገር ውስጥ ጥንካሬዎቻችን ጋር በማዋሃድ የሚለካ ውጤት እናመጣለን” ሲሉ የኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ኢፋ ሙለታ (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት የቻይና ልዑክ ኃላፊ አምባሳደር ጂያንግ ፌንግ ቤጂንግ በአፍሪካ 20 የግብርና ቴክኖሎጂ ማዕከላትን በማቋቋም ከአንድ ሚሊዮን በላይ አነስተኛ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረጓን ገልጸዋል፡፡
ስድስቱ ፕሮጀክቶች፦
የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የሩዝ ምርት ስርዓት በጋራ መገንባት፣
ለከፍተኛ የበቆሎ ምርትና ቅልጥፍና አጠቃላይ ቴክኖሎጂዎችን ማልማትና ማስተዋወቅ፣
በጥጥ እርባታ እና አረንጓዴ ምርት ቴክኖሎጂዎች ላይ ትብብር፣
ዘላቂ የእንስሳት ምርት እና በሽታ መከላከልና ቁጥጥርን ማቀናጀት፣
የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የካሳቫን ጥራት ማሻሻል እና ቅልጥፍናን ለማሳደግ የትብብር ምርምር፣
በአካባቢ ማህበረሰቦች በቴክኖሎጂ የተደገፈ የድህነት ቅነሳ እና ልማት ማስፋት፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X