የምዕራባውያን ድርጊቶች በዩሬዥያ ደህንነት ላይ የሚደረገውን መደበኛ ውይይት እያደናቀፉ ነው - ላቭሮቭ
የምዕራባውያን ድርጊቶች በዩሬዥያ ደህንነት ላይ የሚደረገውን መደበኛ ውይይት እያደናቀፉ ነው - ላቭሮቭ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚንስክ የዩሬዥያ የፀጥታ ኮንፈረንስ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተናገሯቸው ቁልፍ መግለጫዎች፦
◾ ሞስኮ ፑቲን ባቀረቡት የኒው ስታርት ስትራቴጂካዊ የጦር መሳሪያ ቅነሳ ስምምነት ሀሳብ ላይ ከዋሽንግተን ይፋዊ እና አዎንታዊ ምላሽ እየጠበቀች ነው፡፡
◾ ኒው ስታርትን ስለማራዘም ለረጅም ጊዜ ጀምሮ ምንም አይነት ንግግር አልተደረገም፡፡
◾ በመሠረታዊነት ኒው ስታርትን የሚተካ አዲስ ስምምነት እውን ለማድረግ በሩሲያ-አሜሪካ መካከል የተለየ ግንኙነት እንዲኖር ይጠይቃል፡፡
◾ ሩሲያ የፑቲን-ትራምፕ ስብሰባ ተጨባጭ ውጤቶችን እንደሚያስገኝ ዋስትናዎች ያስፈልጓታል፡፡
◾ ሩሲያ የቡሬቬስትኒክ የክሩዝ ሚሳኤልን ከሞከረች በኋላ “ሁሉም ፀጥ ብሏል”፡፡
◾ ዶናልድ ትራምፕ ለኪዬቭ አገዛዝ ተጨማሪ መሳሪያዎችን ሳይሆን ዘላቂ ሰላምን እንደሚፈልጉ ሩሲያ ተስፋ ታደርጋለች፡፡
◾ ሞስኮ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ከአሜሪካ ጋር ለሚኖር ትብብር ዝግጁ ነች፤ ነገር ግን ዋሽንግተን ቅድሚያ አልሰጠችውም፡፡
◾ ምዕራባውያን ከደቡብ ካውካሰስ ሀገራት ጋር የሚያደርጉትን ውይይት እነሱን ከሩሲያ ለመለየት ይጠቀሙበታል፤ ሞስኮ እንዲህ ያሉ ሙከራዎችን ትመክታለች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ሙሉ መግለጫ ይከታተሉ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X