የኢትዮጵያ የጽሑፍ ቅርስ አስመዝጋቢ ብሔራዊ ኮሚቴ በይፋ ሥራውን ጀመረ
15:10 28.10.2025 (የተሻሻለ: 15:14 28.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የጽሑፍ ቅርስ አስመዝጋቢ ብሔራዊ ኮሚቴ በይፋ ሥራውን ጀመረ
በአዲስ መልክ የተቋቋመው ኮሚቴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የዓለም ትውስታ የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን የሀገሪቱን የእጅ ጽሑፎች፣ መዛግብት፣ ታሪካዊ ሰነዶች እና የቃል ወጎች የመጠበቅ ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡
የብሔራዊ ኮሚቴው ዋነኛ ተግባራት፦
ብሔራዊ የሰነድ ቅርስ መዝገብ ማዘጋጀት፡፡
በትውስታ ጥበቃ ዙሪያ የሚደረጉ ብሔራዊ ተነሳሽነቶችን ያስተባብራል፡፡
የኢትዮጵያን ቅርሶች በዩኔስኮ የዓለም ትውስታ መዝገብ ውስጥ እንዲመዘገቡ ያግዛል፡፡
የሀገሪቱ የጽሑፍና የቃል ቅርሶች ለትውልዶች እንዲጠበቅ፣ እንዲከበር እና ተደራሽ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
የዓለም የኦዲዮቪዥዋል ቅርስ ቀንን በማስመልከት በተዘጋጀው መርሃ-ግብር ኮሚቴው ሥራ መጀመሩ ይፋ ተደርጓል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X