የአፍሪካ ኅብረት በሱዳን ኤል-ፋሸር የተፈጸሙትን አሰቃቂ ድርጊቶች በማውገዝ፤ ግጭቱ እንዲቆም ጠየቀ
13:27 28.10.2025 (የተሻሻለ: 13:34 28.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ኅብረት በሱዳን ኤል-ፋሸር የተፈጸሙትን አሰቃቂ ድርጊቶች በማውገዝ፤ ግጭቱ እንዲቆም ጠየቀ
ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ በሱዳን እየተባባሰ የመጣው ግጭት፣ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ የጦር ወንጀሎች እና በዘር ላይ ያነጣጠሩ ግድያዎች፤ ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸው መግለፃቸውን የአፍሪካ ኅብረት በመግለጫው አስታውቋል።
ዩሱፍ ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት ሲቪሎችን የመጠበቅ ግዴታ እንዳለባቸው በማስታወስ፤ ወንጀለኞች ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስጠንቅቀዋል።
አስቸኳይ የተኩስ አቁም እና ለህይወት አድን እርዳታ የሚያስችሉ ሰብዓዊ ኮሪደሮች እንዲከፈቱም ጠይቀዋል።
ሊቀመንበሩ "ለሱዳን ቀውስ ወታደራዊ መፍትሄ ሊኖር አይችልም" በማለት፤ ሁሉም ተዋናዮች ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀምሩ አሳስበዋል።
የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ቡድን በዳርፉር የሱዳን ጦር የመጨረሻ ይዞታ የሆነውን የኤል-ፋሸር ዋና መምሪያ እንደተቆጣጠረ እሁድ አስታውቋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎች ከግንቦት 2024 ጀምሮ በፈጥኖ ደራሽ ቡድኑ ከበባ ስር በነበረችውና በረሃብ በተጠቃችው ከተማ ውስጥ ተይዘው እንደሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የአካባቢው ቡድኖች ሪፖርት አድርገዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X