የጆሃንስበርግ ፖሊስ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መረብን በጣጥሶ 58 ኢትዮጵያውያን ታደገ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየጆሃንስበርግ ፖሊስ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መረብን በጣጥሶ 58 ኢትዮጵያውያን ታደገ
የጆሃንስበርግ ፖሊስ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መረብን በጣጥሶ 58 ኢትዮጵያውያን ታደገ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.10.2025
ሰብስክራይብ

የጆሃንስበርግ ፖሊስ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መረብን በጣጥሶ 58 ኢትዮጵያውያን ታደገ

በጆሃንስበርግ በተካሄደ ከፍተኛ ዘመቻ፣ በሊምፖፖ እና በጋውቴንግ ክልሎች መካከል ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ሲያዘዋውር የነበረ ሕገ-ወጥ የወንጀለኛ ቡድን መረብ መበጣጠሱን የጆሃንስበርግ ከተማ የሕዝብ ደህንነት የከንቲባ ምክር ቤት አባል ምግሲኒ ትሽዋኩ አሳውቀዋል።

በትክክለኛ መረጃ በመመራት፣ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣ ቡድን በምሥራቅ ታውን በሚገኝ የተጠረጠረ መጋዘን ላይ ባካሄደው ድንገተኛ ፍተሻ፣ በተጨናነቀና ኢ-ሰብአዊ በሆነ ሁኔታ ታጭቀው ተይዘው የነበሩ 58 ተጎጂዎችን ታድጓል።

  በድንገተኛ ፍተሻው ወቅት ሦስት የውጭ አገር ዜጎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ይህ ቡድን ተጎጂዎችን ከደቡብ አፍሪካ ማክዶ ግዛት ዚምባብዌ ድንበር አቅራቢያ ወደ ሚገኘው ሊምፖፖ ግዛት በማጓጓዝ በከተማው ውስጥ ወደ ተደበቁ ስፍራዎች ያዘዋውር እንደነበር ይታመናል። ይህ እርምጃ በቡድኑ ላይ ትልቅ ጉዳት ማድረሱን ያመለክታል።

የፓሊስ መኮንኖች በርካታ ሞባይል ስልኮችን፣ የጥገኝነት መጠየቂያ ሰነዶችን፣ ለወንጀለኛ ቡድኑ አገልግሎት ስትሰጥ የነበረች ሱዙኪ ሰሌሪዮ መኪና እና የውሸት  ሽጉጥ ጨምሮ ቁልፍ ማስረጃዎችን ማግኘት ችለዋል።

መርማሪዎች አሁንም በኔትወርኩ ውስጥ ያሉ ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን እየተከታተሉ በመሆኑ፣ ተጨማሪ እስራት ሊከተል እንደሚችል ገልጸዋል። 58ቱ ሰዎች ደህንነታቸው  ወደሚጠበቅበት ስፍራ የደረሱ ሲሆን፣ የወንጀል ማጓጓዣ መስመርም ከመነሻው ተቆርጧል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የጆሃንስበርግ ፖሊስ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መረብን በጣጥሶ 58 ኢትዮጵያውያን ታደገ - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የጆሃንስበርግ ፖሊስ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መረብን በጣጥሶ 58 ኢትዮጵያውያን ታደገ - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0