የሰው ሠራሽ አስተውሎት የመረጃ ግብዓቶች አፍሪካን በአግባቡ ማሳየት አለባቸው - የዝምባቡዌ የፈጠራ ባለሙያ

ሰብስክራይብ

የሰው ሠራሽ አስተውሎት የመረጃ ግብዓቶች አፍሪካን በአግባቡ ማሳየት አለባቸው - የዝምባቡዌ የፈጠራ ባለሙያ

ታቴንዳ ሙሶድዛ፣ ችግር ፈቺ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሥርዓቶችን ለማስፋት፣ የቴክኖሎጂው የመረጃ አቅርቦት የገጠሩን ማኅበረሰብ እውነታ የዘነጋ አለመሆኑን ማረጋገጥ እንደሚገባ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል፡፡

"የመረጃ ስብስቦቹ ቴክኖሎጂ እምብዛም ባልተስፋፋባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖችን የሚወክሉ መሆን አለባቸው። ይህም ሁሉንም አስፈላጊ መረጃዎች በመጠቀም ችግሮቻቸውን ለመፍታት ያግዛል።" ብለዋል።

የፈጠራ ባለሙያው የሚሰበሰቡ መረጃዎች ወደ አውሮፓ የሚላኩ ተጨማሪ ጥሬ ዕቃዎች እንዳይሆኑ ስልቶቸን መንደፍ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0