የደቡብ ለደቡብ ትብብር ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ አገራት መካከል የእውቀት ልውውጥን ያመቻቻል - የፋኦ ምክትል ዋና ዳይሬክተር
20:02 27.10.2025 (የተሻሻለ: 20:04 27.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የደቡብ ለደቡብ ትብብር ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ አገራት መካከል የእውቀት ልውውጥን ያመቻቻል - የፋኦ ምክትል ዋና ዳይሬክተር
ሩሲያ የአፍሪካ አገራት የቴክኖሎጂ አቅምን በጋራ መፍጠር እንዲችሉ፣ እውቀትን፣ ሳይንስን እና የፈጠራ ሥራዎችን እንዲሠሩ እየረዳቻቸው ነው ሲሉ የተመድ የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ረዳት ዋና ዳይሬክተር እና የአፍሪካ ቀጣናዊ ተወካይ አበበ ኃይለ ገብርኤል በዓለም አቀፉ የሳይንስ ይፋዊ ኤግዚቢሽን ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
አሁንም ራሷን ለመመገብ እየታገለች ያለችው አፍሪካ ግብርናዋን ማዘመን እንደሚገባት አጽናኦት ሰጥተዋል፡፡
"መፍትሄው የግብርና ምርታማነትን መጨመር ነው ... ይህም ማለት በአነስተኛ ግብዓት ብዙ ምርት ማግኘት። ይህንን ደግሞ ሳይንስን፣ ቴክኖሎጂንና ፈጠራን ተግባራዊ ሳናደርግ ማግኘት አንችልም"
አበበ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች የአፍሪካ አገራት ያለው የወጣት ኃይል ወደ ሥራ ማስገባት መቻል አለብን ሲሉ አክለዋል።
" ... ግብርናውን ዘመናዊ ካደረግነው፤ ዘመናዊ ማድረግም አለብን፤ ወጣቱ በጉጉት ዘሎ በመግባት ተጠቃሚ ይሆናል" ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት እጅግ ከፍተኛ አፈፃፀም ማሳየቷን አስመልክቶም፣ የስንዴ ምርት ኢትዮጵያን ከአገር ወስጥ ፍላጎት በተጨማሪ ከሰፊው የአፍሪካ የውጭ ንግድም ተጠቃሚ እንድትሆን ያስችላታል ብለዋል።
በሰው ሠራሽ አስተሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X