“የአዕምሮ እድገት ዉሱንነት ያለባቸው ልጆች እንደማንኛውም ሰው ሕይወት ይገባቸዋል” - የዲቦራ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ

ሰብስክራይብ

“የአዕምሮ እድገት ዉሱንነት ያለባቸው ልጆች እንደማንኛውም ሰው ሕይወት ይገባቸዋል” - የዲቦራ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ

ቤኪ አባዱላ በ100ኛው የሩሲያ የሕዝብ ዲፕሎማሲ ቀን አከባባር ላይ እየተሳተፈች ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ የጋራ ጥረት ፎረም ላይ "መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ዲፕሎማሲ" በሚል ርዕስ ንግግር እንደምታደርግ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግራለች።

"ሩሲያ ውስጥ ካሉ ተመሳሳይ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር አጋርነት ለመፍጠር፣ እርዳታ ለማግኘት፣ የእውቀት ሽግግር ለማግኘት፣ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ተዘጋጅተናል ... ሩሲያ ውስጥ የአዕምሮ እድገት ዉሱንነት ላለባቸው ልጆች የሚደረገውን እንክብካቤ እና የሚሰጣቸውን ሥልጠና ኢትዮጵያ ላይ እንዲሰጣቸው ለማድረግ ነው የመጣሁት" ስትል የሁነቱን አስፈላጊነት ገልጻለች።

ፋውንዴሽናቸው ውስጥ ልዩ ልዩ የአዕምሮ እድገት ውሱኑነት ያለባቸው ከ2 ሺህ በላይ ልጆች እንዳሉ በመግለጽም፣ ልጆቹ ከተማሩ፣ ሥልጠናዎችን ካገኙ የራሳቸውን ሕይወት መምራት እንደሚችሉ አብነት በመጥቀስ አስረድታለች፡፡

“... ወደ ትምህርት እንዲገቡ፣ ትምህርት ከተማሩ በኋላ ደግሞ ሥራ እንዲቀጠሩ እናደርጋለን። እስካሁን ወደ 20 ልጆች ገደማ የተቀጠሩ አሉን፡፡ አስራ አንዱ በዲቦራ ፋውንዴሽን ነው፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ኢትዮጵያን ኤርላይንስ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ አዋጭ፣ ሆላንድ ዴይ ቀጥሮልናል።”

ቤኪ አባዱላ የሩሲያ መንግሥት ለኢትዮጵያ ተማሪዎች ያደረገውን እና እያደረገ ያለውን ነፃ የትምህርት ዕድሎች እና ሌሎች ድጋፍ በማንሳት ምስጋና አቀርባለሁ ብላለች።

ቤኪ በሞስኮ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ያደረገችውን ቆይታ ይመልከቱ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0