#viral | በሞስኮ ሰማይ ላይ የታየው ምስጢራዊ አረንጓዴ የእሳት ኳስ፤ የጠፈር አለት ስባሪ ወይስ የጠፈር ቆሻሻ?

ሰብስክራይብ

#viral | በሞስኮ ሰማይ ላይ የታየው ምስጢራዊ አረንጓዴ የእሳት ኳስ፤ የጠፈር አለት ስባሪ ወይስ የጠፈር ቆሻሻ?

ዛሬ ማለዳ ላይ ሞስኮ አቅራቢያ የተቀረፁ እና በማኅበራዊ የትስስር ገፆች ላይ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኙ ቪዲዮዎች የሚያሳዩት ትንሽዬ ሜትሮይት (የጠፈር አለት) ወይም የጠፈር ቆሻሻ ሊሆን እንደሚችል፣ የሩሲያ የጠፈር ምርምር ኢንስቲትዩት የፀሐይ አስትሮኖሚ ላቦራቶሪ ኃላፊ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ኃላፊው እንዳብራሩት፣ "ይህ ምናልባት 10 ሴንቲሜትር የሚሆን ሜትሮይት ሊሆን ይችላል... ሰዎች ከ5 እስከ 10 ሴ.ሜ የሚደርሱ ድንጋዮች እንዲህ ያለ ብርሃናማ መስመር መፍጠር መቻላቸው ብዙ ጊዜ ይገርማቸዋል፤ ግን እውነታው ይህ ነው።"

አረንጓዴው ቀለም የተፈጠረው አብዛኛውን ጊዜ በእንደነዚህ ዓይነት አካላት ውስጥ በሚገኝ ከፍተኛ የኒኬል ይዘት ምክንያት ነው ሲሉ ሳይንቲስቱ ገልጸዋል። አክለውም፣ ይህ አካል በከባቢ አየር ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተቃጥሎ አልቆ ሊሆን ይችላል ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0