በአዲስ አበባ በ2ተኛው ምዕራፍ የተሠሩ አራት የኮሪደር ልማት መስመሮች ለአገልገሎት ከፍት ተደርጉ
17:02 27.10.2025 (የተሻሻለ: 17:04 27.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአዲስ አበባ በ2ተኛው ምዕራፍ የተሠሩ አራት የኮሪደር ልማት መስመሮች ለአገልገሎት ከፍት ተደርጉ
ከመስቀል አደባባይ - መገናኛ - ሳዉዝ ጌት፣ ከአንበሳ ጋራዥ -ጎሮ ፣ ከአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬሽን ማዕከል - ጎሮ -ቦሌ ቪአይፒ ተርሚናል እንዲሁም ከሳር ቤት - ጀርመን አደባባይ - ጋርመንት - ፉሪ አደባባይ መስመሮች ናቸው፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ “የከተማችን ነዋሪዎች... ለጋራ ልማት በመተባበር፣ ቡና እያፈላ፣ ውሃ እያቀረበ ለልማት ሥራዉ ዉጤታማነት ላሳየዉ ከፍተኛ ድጋፍ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።” ሲሉ በማኅበራዊ የትስስር ገጻችው ላይ ጽፈዋል፡፡
በ1ኛ እና በ2ኛ ዙር የኮሪደር ልማት ሥራዎች ከተጠናቀቁ መሠረተ-ልማቶች መካከል፦
342 ኪ.ሜ የእግረኛ፣ 185 ኪ.ሜ የተሽከርካሪ እና 241 ኪ.ሜ የሳይክል መንገዶች ተሠርተዋል፡፡
101 የሕጻናት መጫወቻዎች፣ 155 የስፓርት ማዘውተሪያዎች እና 210 የሕዝብ መፀዳጃዎች ተገንብተዋል።
153 ዘመናዊ ፓርኪንግ እና ተርሚናሎችም ለአግልግሎት በቅተዋል፡፡
ለፕሮጀክቶቹ መሳካት አስተዋጻኦ ላበረከቱ "ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች እና ሠራተኞች፣ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች፣ ማኅበራት፣ በጎ ፈቃደኞች እና ሌሎችም" ውቅና ተሰጥቷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X