የሩሲያ ኃይሎች በኩፕያንስክ እና በክራስኖአርሜይስክ የተከበቡትን የዩክሬን ቡድኖች መደምሰሳቸውን ቀጥለዋል - መከላከያ ሚኒስቴር
16:07 27.10.2025 (የተሻሻለ: 16:14 27.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ ኃይሎች በኩፕያንስክ እና በክራስኖአርሜይስክ የተከበቡትን የዩክሬን ቡድኖች መደምሰሳቸውን ቀጥለዋል - መከላከያ ሚኒስቴር
በልዩ ወታደራዊ ዘመቻው የኩፕያንስክ አካባቢ፣ የዩክሬን ክፍሎች ከክበባው ወደ ኦስኮል ወንዝ ቀኝ ዳርቻ ለመውጣት ያደረጓቸው አራት ሙከራዎች ተመክተዋል፤ በዚህም እስከ 50 የሚደርሱ የዩክሬን ወታደሮች መገደላቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በክራስኖአርሜይስክ አካባቢ ደግሞ በዛሬው ዕለት ከ60 በላይ የዩክሬን ወታደሮች መገደላቸውን ሚኒስቴሩ አክሎ ገልጿል።
በትናንትናው ዕለት የሩሲያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ቫሌሪ ጌራሲሞቭ ለፑቲን ባቀረቡት ሪፖርት፣ የሩሲያ ጦር በክራስኖአርሜይስክ ጠላትን የመክበብ ሥራውን እያጠናቀቀ ሲሆን፣ በኩፕያንስክ ደግሞ በኦስኮል ወንዝ ላይ ያለውን መሻጋሪያ መያዙን ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X