በዘንድሮ የመኸር ወቅት 177 ሚሊዮን ኩንታል የስንዴ ምርት ይጠበቃል - የግብርና ሚኒስትር
15:45 27.10.2025 (የተሻሻለ: 15:54 27.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በዘንድሮ የመኸር ወቅት 177 ሚሊዮን ኩንታል የስንዴ ምርት ይጠበቃል - የግብርና ሚኒስትር
ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ በስንዴ እየለማ ከሚገኘው 4.5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ወስጥ 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሄክታሩ በኩታገጠም የአስተራረስ መንገድ እየለማ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በዘንድሮ የመኸር ወቅት በአገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ሰብሎች ከተሸፈነው 20 ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታር መሬት 653 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅም አክለዋል።
ኢትዮጵያ በየዓመቱ በአማካይ እስከ 1 ቢሊዮን ዶላር በማውጣት የስንዴ ምርት ከውጭ ስታስገባ እንደነበር ያስታወሱት ሚኒስትሩ፤ ባለፉት ዓመታት ስንዴን በበጋና በክረምት በስፋት በማልማት የውጭ ምንዛሬ ወጪውን ማዳን መቻሉንም ተናግረዋል።
የአየር ንብረት የሚቋቋም የስንዴ እሴት ሰንሰለት ልማት ፕሮጀክት፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክ እና ከመንግሥት በተገኘ በጀት በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በሶማሌ እና በአፋር ክልሎች በ76 ወረዳዎች እየተተገበረ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
/