“አሜሪካ ጥቁር ሕጻናትን ለማሳደግ አስፈሪ አገር ናት” - ኑሮዋን በኢትዮጵያ ያደረገችው ጥቁር አሜሪካዊት

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ“አሜሪካ ጥቁር ሕጻናትን ለማሳደግ አስፈሪ አገር ናት” - ኑሮዋን በኢትዮጵያ ያደረገችው ጥቁር አሜሪካዊት
“አሜሪካ ጥቁር ሕጻናትን ለማሳደግ አስፈሪ አገር ናት” - ኑሮዋን በኢትዮጵያ ያደረገችው ጥቁር አሜሪካዊት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.10.2025
ሰብስክራይብ

“አሜሪካ ጥቁር ሕጻናትን ለማሳደግ አስፈሪ አገር ናት” - ኑሮዋን በኢትዮጵያ ያደረገችው ጥቁር አሜሪካዊት

ሥራ ፈጣሪዋ ፕሪንስስ ዋሲሁን በተለይም ጥቁር ልጆችን እንደምታሳድግ እናት፣ በአሜሪካ ስላጋጠማት የዘረኝነት እንቅስቃሴ እና ስሜታዊ ጫና ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግራለች።

ትውልድና እድገቷ በአሜሪካ የሆነው ፕሪንሰስ እንደገለፀችው በአሜሪካ፣ ንፁኅን ሕጻናትም ሳይቀሩ በቆዳ ቀለማቸው ምክንያት እንደ ስጋት ይታያሉ።

" የኔ ጣፋጭ፣ አስተዋይ ልጆችን አደጋ አድርጎ በሚያያቸው በዚህ አይነቱ ዓለም ውስጥ እንዲያድጉ አልፈልግም፡፡" ስትል ተናግራለች።

ፕሪንሰስ ዋሲሁን ብዙ አፍሪካ አሜሪካውያን የአፍሪካ ማንነታቸውን እንዳይቀበሉ የሚያደርጉ በርካታ የሥነ-ልቦና መሰናክሎችንም አሉ ስትል በምዕራባውያኑ የሚዘወሩት ሚዲያዎች ዋነኞቹ መሆናቸውን ጠቅሳለች።

“አሜሪካውያን ስለሆንን 'የተሻልን ነን' ብለን እናስባለን፤ ግን አሁንም ነጻ አይደለንም” በማለት አጽናኦት ሰጥታለች።

አሁን ከባለቤቷ እና ከልጆቿ ጋር ኑሮን በኢትዮጵያ ያደረገችው ፕሪንሰስ፣ ልጆቻቸው በአሜሪካ ከነበረው የዘረኝነት ጥቃት ሰለባና፣ የጅምላ የጦር መሣሪያ ጥቃት ነፃ ሆነው፣ ይበልጥ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ከቅርስና ባሕላቸው ጋር የተገናኙ መሆናቸውን ገልፃለች።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0