ስሎቫኪያ ዩክሬንን ለመደገፍ ለሚደረገው የአውሮፓ ሕብረት የገንዘብ ድጋፍ 'አልፈቅድም ' ብላለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ፊኮ

ሰብስክራይብ

ስሎቫኪያ ዩክሬንን ለመደገፍ ለሚደረገው የአውሮፓ ሕብረት የገንዘብ ድጋፍ 'አልፈቅድም ' ብላለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ፊኮ

"የመንግሥት መሪ እንደመሆኔ መጠን ዩክሬን ጦርነቱን እና ወታደራዊ ወጪዎችን እንድትቋቋም የመርዳት ዓላማ ባለው ማንኛውም የገንዘብ ድጋፍ መርሃ ግብር ውስጥ ስሎቫኪያ እንድትሳተፍ አልፈቅድም፡፡" ሲሉ ሮበርት ፊኮ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ዩክሬን የመክፈል አቅም "የላትም" በማለት የአውሮፓን የጋራ መዋጮዎችን ወይም የብድር ዋስትናዎችን ጨምሮ የቀረቡትን ምክረ ሐሳቦች ተችተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ "1.4 ቢሊዮን ዩሮ (1.63 ቢሊዮን ዶላር) ዋስትናችን ምን ሊሆን እንደሚችል ታውቃላችሁ? ለዩክሬን ወታደራዊ ፍላጎቶች የ1.4 ቢሊዮን ዩሮ ዋስትና እንድፈርም ነው የሚጠበቀው?" ሲሉ ጠይቀዋል።

አርብ ዕለት ፊኮ ስሎቫኪያ ለዩክሬን የሰብዓዊ ዕርዳታ እየሰጠች መሆኗን ገልጸው፣ ነገር ግን በእርሳቸው አመራር ስር ከአገሪቱ በጀት "አንድ ሳንቲም እንኳን" ለኪዬቭ ወታደራዊ ወጪ እንደማይውል አፅንዖት ሰጥተዋል።

እ.ኤ.አ. ከየካቲት 2022 ጀምሮ ሩሲያ በዩክሬን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረች ወዲህ የምዕራባውያን አገራት ለኪዬቭ የሚሰጡትን ወታደራዊ ድጋፍ አጠናክረዋል። ሩሲያ በተደጋጋሚ እንደዚህ ዓይነቶቹ የጦር መሣሪያዎች አቅርቦቶች ለዩክሬን መፍትሔ እንቅፋት እንደሚፈጥሩ እና የኔቶ አገራትን በቀጥታ ወደ ግጭቱ እንደሚስቡ አሳውቃለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0