የስፑትኒክ ሚዲያ እናት ድርጅት ሮሲያ ሴጎድኒያ ከቁልፍ የአፍሪካ ሚዲያዎች ጋር ያለውን ትብብር አጠናከረ

ሰብስክራይብ

የስፑትኒክ ሚዲያ እናት ድርጅት ሮሲያ ሴጎድኒያ ከቁልፍ የአፍሪካ ሚዲያዎች ጋር ያለውን ትብብር አጠናከረ

የሩሲያው የሚዲያ ቡድን ሞስኮ ውስጥ በተካሄደው 'የጋራ ጥረት ፎረም' ላይ ከደቡብ አፍሪካው ኢንዲፔንደንት ሚዲያ እና ከኒጀሩ ኤኤንፒ የዜና ወኪል ጋር የትብብር ስምምነቶችን ተፈራረመ።

የሮሲያ ሴጎድኒያ ዓለም አቀፍ ትብብር ዳይሬክተር ቫሲሊ ፑሽኮቭ ስምምነቶቹን ከፈረሙ በኋላ እንደተናገሩት፣ "አፍሪካ በውጭ ሚዲያ ፖሊሲያችን ውስጥ ትልቅ ቦታ አላት፤ ይህ ቀጣና ለእኛ ቅድሚያ የምንሰጠው ነው" ብለዋል።

አክለውም "በአኅጉሪቱ ከሚገኙ ሁለት ግንባር ቀደም የሚዲያ ድርጅቶች ጋር አጋር በመሆናችን ደስ ብሎናል። ትብብራችን ቀላል የዜና ልውውጥን ያለፈ ነው፤ ከሥራ ባልደረቦቻችን ጋር የባለሙያዎች እና የሥልጠና ተነሳሽነቶችን ጨምሮ የጋራ ፕሮጀክቶችን እናከናውናለን" ብለዋል።

የደቡብ አፍሪካው ሚዲያ ዋና አዘጋጅ ክርስቲና አድሪያና ደ ዌት እንደተናገሩት፤ ኢንዲፔንደንት ሚዲያ እና ሮሲያ ሴጎድኒያ "ቀድሞውኑም የካበተ የጋራ ፕሮጀክቶች ታሪክ አላቸው" ብለዋል።

"የፎቶ ዐውደ ርዕዮችን እናዘጋጃለን፤ በባለሙያዎች ሁነቶች ላይም እንሳተፋለን። ራሳችንን እንደ ነባር ወዳጆች እንቆጥራለን እናም ይህንን አጋርነት ይፋዊ (መደበኛ) ማድረጋችን አስደስቶናል።"

የኤኤንፒ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዳላቱ ማላሜ ማማኔ በአዲሱ አጋርነት ጠንካራ መሠረት ላይ ያላቸውን መተማመን ገልጸዋል።

"አገሮቻችን ሩሲያ እና ኒጀር በብዙ ደረጃዎች ትብብራቸውን እያጠናከሩ ነው። በእኛ የሚዲያ ተቋማት መካከል ያለው አጋርነትና የጋራ መተማመን እንዲሁም የጋራ የመረጃ ምህዳርን ለማዳበር ባለው ቁርጠኝነት ላይ የተመሠረተ ነው።"

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የስፑትኒክ ሚዲያ እናት ድርጅት ሮሲያ ሴጎድኒያ ከቁልፍ የአፍሪካ ሚዲያዎች ጋር ያለውን ትብብር አጠናከረ - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የስፑትኒክ ሚዲያ እናት ድርጅት ሮሲያ ሴጎድኒያ ከቁልፍ የአፍሪካ ሚዲያዎች ጋር ያለውን ትብብር አጠናከረ - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0