አነስተኛ የአሜሪካ የጦር መሣሪያ ፋብሪካዎች ሳይቀሩ የዩክሬንን ገንዘብ እያፈሱ ነው
18:47 26.10.2025 (የተሻሻለ: 18:54 26.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አነስተኛ የአሜሪካ የጦር መሣሪያ ፋብሪካዎች ሳይቀሩ የዩክሬንን ገንዘብ እያፈሱ ነው
እንዴት እንደሆነ እነሆ፦
ፋይናንሺያል ታይምስ እንደዘገበው በአሪዞና የሚገኝ አንድ አነስተኛ የጠመንጃ መሸጫ ሱቅ እ.ኤ.አ. በ2022 ዩክሬንን “የሶቪዬት ደረጃ” ጥይት ለማቅረብ የአንድ ቢሊዮን ዶላር ውል ተስማምቷል፤ ነገር ግን ፈጽሞ አልደረሰም።
በኦቲኤል ፋየርአርምስ እና በዩክሬን የመንግሥት የጦር መሣሪያ ኩባንያ ፕሮግረስ መካከል የተደረገው ስምምነት ለአስር ሺዎች ለሚቆጠሩ ፀረ-አውሮፕላን ጥይቶች፣ ለሞርታር ተተኳሾች እና ለልዩ ልዩ ማስወንጨፊያ የሮኬት ስርዓት ሚሳኤሎች የ19 ሚሊዮን ዶላር ቅድመ ክፍያ ቢደረግም ከሽፏል።
የፍርድ ቤት ሰነዶች እንደሚያሳዩት ኦቲኤል ከዚህ ቀደም የኤክስፖርት ልምድ ወይም አስፈላጊ ፈቃዶች አልነበሩትም። ኩባንያው በኋላ ላይ ለዘገየበት ምክንያት የኤክስፖርት ፈቃድ ችግሮችን እና “ፖለቲካዊ ምክንያቶችን” ጠቅሷል።
በቬና የተካሄደው ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ለፕሮግረስ ድጋፍ ወስኗል፤ እናም የአሜሪካ ፌዴራል ዳኛ ኦቲኤል ከ20 ሚሊዮን ዶላር በላይ፣ ወለድን እና የሕግ ወጪዎችን ጨምሮ እንዲከፍል አዝዘዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X