የአፍሪካ ዓለም አቀፍ ሚና በፖለቲካዊ ዲፕሎማሲ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚ ኃይልም የሚመረኮዝ ነው - የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
18:30 26.10.2025 (የተሻሻለ: 18:34 26.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ዓለም አቀፍ ሚና በፖለቲካዊ ዲፕሎማሲ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚ ኃይልም የሚመረኮዝ ነው - የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ በአዲስ አበባ በተካሄደው የጣና ፎረም መድረክ ላይ እንደተናገሩት፤ አኅጉሪቱ እውነተኛ ዕድገት ምኞቷ “ያለኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ እምነት የሚጣልበት አይሆንም” ብለዋል።
“የአፍሪ ልህቀት የሚመጣው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ወይም በፖለቲካ ሰዎች ብቻ ሊሆን እንደማይችል መቀበል አለብን። የስኬታችን እውነተኛ መወሰኛ ኢኮኖሚው ይሆናል" ሲሉ ተናግረዋል።
አፍሪካ በበጎ ፈቃደኛ የውጭ ባለሀብቶች ላይ ብቻ መደገፍ እንደሌለባት፣ ይልቁንም የአገር ውስጥ የሥራ-ፈጣራ እና በአፍሪካ አገራት መካከል ያለውን ኢንቨስትመንት ማጎልበት እንዳለባት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተዋል። ለዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድን እንዲሁም የኬንያ እና የናይጄሪያ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ያደረጉትን ኢንቨስትመንት እንደ ስኬታማ አብነት ጠቅሰዋል።
“ይህ የኢንቨስትመንት አይነት ኢኮኖሚያዊ ቁመናችንን ለማሳደግ እንዲሁም ብልጽግናን ለማምጣት ወሳኝ ነው” ሲሉም ተደምጠዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ የአፍሪካ አገራት የራሳቸውን ቦታ በመያዝ የዓለም አቀፍ እድገትና ፈጠራ የወደፊት አንቀሳቃሾች እንዲሆኑ በማሳሰብ፣ በወጣቶች የአቅም ግንባታና ቴክኖሎጂ ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X