የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በኤል ፋሸር የሚገኝ ቁልፍ የወታደራዊ ዋና መሥሪያ ቤት መቆጣጠረራቸውን አስታወቁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በኤል ፋሸር የሚገኝ ቁልፍ የወታደራዊ ዋና መሥሪያ ቤት መቆጣጠረራቸውን አስታወቁ
የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በኤል ፋሸር የሚገኝ ቁልፍ የወታደራዊ ዋና መሥሪያ ቤት መቆጣጠረራቸውን አስታወቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.10.2025
ሰብስክራይብ

የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በኤል ፋሸር የሚገኝ ቁልፍ የወታደራዊ ዋና መሥሪያ ቤት መቆጣጠረራቸውን አስታወቁ

የሱዳን ጦር ስለመያዙ ገና ማረጋገጫ አልሰጠም። ሆኖም ከአንድ ቀን በፊት በኤል ፋሸር ላይ የተሰነዘሩ በርካታ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጥቃቶችን መክቶ መመለሱን ገልጿል።

ፋጥኖ ደራሽ ኃይሉ፣ ለ18 ወራት ያህል የሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ የሆነችውን እና የሠራዊቱ በዳርፉር ክልል የመጨረሻዋ ዋና ምሽግ የሆነችውን ኤል ፋሸርን ከብቦ ቆይቷል።

በቅርቡ በተባበሩት መንግሥታት የተቋቋመ ተልዕኮ እንዳስታወቀው፣ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በኤል ፋሸር ከበባው ወቅት ሰፊ የሆነ ረሃብን እና በሲቪሎች ላይ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃቶችን ያስከተለ በርካታ የሰብአዊነት ወንጀሎችን ፈጽሟል።

የአካባቢው የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ ኃይሉ የክልሉን ሌሎች አካባቢዎች ሲቆጣጠር የታየውን አዝማሚያ በመድገም ኤል ፋሸርን መቆጣጠሩ ወደ ሰፊ የጎሳ ጥቃቶች ሊመራ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0