ኢትዮጵያ በቀጥታ ወደ ቀይ ባሕር የሚያመራ አዲስ የባቡር መስመር ለመገንባት ማቀዷ ተዘገበ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በቀጥታ ወደ ቀይ ባሕር የሚያመራ አዲስ የባቡር መስመር ለመገንባት ማቀዷ ተዘገበ
ኢትዮጵያ በቀጥታ ወደ ቀይ ባሕር የሚያመራ አዲስ የባቡር መስመር ለመገንባት ማቀዷ ተዘገበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.10.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በቀጥታ ወደ ቀይ ባሕር የሚያመራ አዲስ የባቡር መስመር ለመገንባት ማቀዷ ተዘገበ

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን (ኢምባኮ) ሰሜን ኢትዮጵያን ከታጁራ፣ ከአሰብ እና ከምፅዋ የቀይ ባሕር ወደቦች ጋር ለማገናኘት የሚያስችል ደረጃውን የጠበቀ የባቡር መስመር እቅድ ይፋ አድርጓል ሲል አገር ውስጥ የግል ጋዜጣ አስነብቧል፡፡

1.58 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጪ ይጠይቃልም ተብሏል፡፡

ሚዲያው ተመለከትኩት ያለው ሰነድ፣ 216 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚኖረው የወልድያ-ሐራ ገበያ-መቐለ ነጠላ የባቡር መስመር፣ የባሕር በር ለማግኘት መንግሥት እያደረገ ያለውን መጠነ-ሰፊ ዘመቻ የሚያስፈጽም መሆኑን ያመላክታል።

ሰነዱ "የባቡሩ መስመሩ ኢትዮጵያን ከታጁራ፣ አሰብ እና ምፅዋ ወደቦች ጋር ያገናኛል" ሲል እንደሚያጠቃልል ጋዜጣው ጽፏል።

እንደ ሚዲያው እቅዶቹ ማክሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል በተካሄደው፣ ብሔራዊ የባቡር ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ወቅት በቀረበው የ21 ገጽ የኩባንያ ሪፖርት ላይ ተዘርዝረዋል።

ፎቶ፦ የወልድያ-ሐራ ገበያ-መቐለ የባቡር ፕሮጀክት

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0