ሩሲያ ለፍትሐዊ እና ለእኩልነት አጋርነት ሁልጊዜም ዝግጁ ናት ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ

ሰብስክራይብ

ሩሲያ ለፍትሐዊ እና ለእኩልነት አጋርነት ሁልጊዜም ዝግጁ ናት ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ

“ሩሲያ በሰፊና ከፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ በሆነ ዓለም አቀፍ ትብብር ላይ ፍላጎት ያላት ዘመናዊ መንግሥት ሆና ማደጓን ቀጥላለች” ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሞስኮ በተካሄደው የጋራ ጥረት ጉባኤ ላይ ንግግር አድርገዋል።

ሩሲያ በርካታ እውነተኛ እና አስተማማኝ ወዳጆች እንዳሏት ላቭሮቭ አጽንኦት ሰጥተዋል።

“የዓለም ሁኔታ ውጥረት ውስጥ ባለበት በዚህ ወቅት ወቅት፤ በሳይንስ፣ በባሕል እና በስፖርት ዘርፎች በሚገኙ ሰዎች መካከል የሚደረጉ የግል ግንኙነቶችና ውይይቶች ሁኔታውን ከማሻሻል አንጻር ልዩ ጠቀሜታ አላቸው” ሲሉም አስረድተዋል፡፡

የጋራ ጥረት ጉባኤው እየተካሄደ ያለው በሩሲያ የሕዝብ ዲፕሎማሲ 100ኛ ዓመት ክብረ በዓል አካል የሆኑ ሁነቶች ውስጥ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0