የራማፎሳ ታሪካዊ የደቡብ ምስራቅ እስያ አገራት ማኅበር ጉብኝት ቅኝት፡
የራማፎሳ ታሪካዊ የደቡብ ምስራቅ እስያ አገራት ማኅበር ጉብኝት ቅኝት፡
ጉብኝቱ ደቡብ አፍሪካ ከደቡብ ምሥራቅ እስያ ጋር ያላትን ግንኙነት የሚያሳድግ ነው ተብሏል፡፡
ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከጥቅምት 15 እስከ 18 ድረስ በ47ኛው የደቡብ ምሥራቅ እስያ አገራት ማኅበር የመሪዎች ጉባኤ እና በምስራቅ እስያ የመሪዎች ጉባኤ ላይ የሊቀ-መንበሩ እንግዳ በመሆን ማሌዥያ ተገኝተዋል። እ.ኤ.አ በየካቲት 2018 ፕሬዝዳንትነቱን ከተረከቡ ወዲህ ወደ ማሌዥያ ያደረጉት የመጀመሪያ ይፋዊ ጉብኝት ነው።
በጉብኝታቸው ወቅት ራማፎሳ በተለያዩ ቁልፍ እንቅስቃሴዎች ተሳትፈዋል፡-
🟠 በ2025 ከማኅበሩ የንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ጎን ለጎን በተካሄደው የመሪዎች የውይይት መድረክ ላይ ተሳትፈዋል፤ እንዲሁም የማሌዥያ ስታንዳርድ ቻርተርድ ባንክ የቦርድ አባላትን አግኝተዋል (ቪዲዮ 2)፡፡
🟠 ፕሬዝዳንቱ ማሌዥያ ፑትራጃያ በሚገኘው ይፋዊ የመኖሪያ ስፍራ ፔርዳና ፑትራ ኮምፕሌክስ ሲደርሱ፣ የማሌዥያው ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ቢን ኢብራሂም አቀባበል አድርገውላቸዋል (ቪዲዮ 3)፡፡
🟠 የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት በፔርዳና ፑትራ ኮምፕሌክስ ለእሳቸው በተደረገው የእንኳን ደህና መጡ ሥነ ሥርዓት ላይ ወታደራዊ ዘብ ተመልክተዋል፤ እንዲሁም በይፋዊው መኖሪያ ስፍራ የጎብኚዎች መዝገብ ላይ ፈርመዋል (ቪዲዮ 4)፡፡
🟠 ራማፎሳ እና ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር፣ ከየልዑካን ቡድኖቻቸው ጋር በመሆን የሁለትዮሽ ውይይቶች አድርገዋል። በፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት መግለጫ መሠረት፣ እነዚህ ውይይቶች በግብርና፣ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ እሴት ሰንሰለት ፣ በሴሚኮንዳክተሮች ፣ በመከላከያ ኢንዱስትሪዎች እና በክህሎት ልማት መስኮች የንግድ ልውውጥን በማሳደግ ላይ ያተኮሩ ነበሩ (ቪዲዮ 5)፡፡
🟠 ፕሬዝዳንቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፣ የደቡብ አፍሪካ ግንኙነት ከማሌዥያ ጋር፣ እንዲሁም ከደቡብ ምሥራቅ እስያ እና ከደቡብ ምሥራቅ እስያ አገራት ማኅበር ጋር ያለው ግንኙነት “ለደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ አለው” (ቪዲዮ 6)፡፡
🟠 ፕሬዝዳንት ራማፎሳ በኳላ ላምፑር የስብሰባ ማዕከል በተካሄደው 47ኛው የደቡብ ምሥራቅ እስያ አገራት ማኅበር የመሪዎች ጉባኤ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል፤ በዚያም ከማኅበሩ መሪዎች ጋር የቤተሰብ ፎቶግራፍ ተነስተዋል (ቪዲዮዎች 7 እና 8)፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X