የኢትዮጵያ የግብርና ምርት በ2017 የምርት ዓመት 1.57 ቢሊዮን ኩንታል አድጓል ሲሉ አደም ፋራህ ተናገሩ
14:55 26.10.2025 (የተሻሻለ: 15:04 26.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የግብርና ምርት በ2017 የምርት ዓመት 1.57 ቢሊዮን ኩንታል አድጓል ሲሉ አደም ፋራህ ተናገሩ
ይህ አኃዝ ከሰባት ዓመታት በፊት በ2010 ዓ.ም ከተመዘገበው 306.1 ሚሊዮን ኩንታል ጋር ሲነፃፀር፣ የሰባት እጥፍ ዕድገት ማስመዝገቡን ያመለክታል ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።
አደም ፋራህ ይህ ዕድገት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ አነስተኛ አርሶ አደሮችን በቀጥታ የሚጠቅም በመሆኑ ጥልቅ ማኅበራዊ ተፅእኖ እንዳለው አስምረውበታል።
የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ከሰብል ምርት በተጨማሪ የከብት እርባታውን ዘርፍ ማነቃቃቱን በመጠቆም እንደ ወተት፣ እንቁላል፣ የዶሮ እርባታ እና ዓሳ ምርት እንዲያድግ በማድረግ ለተሻለ የምግብ ዋስትና እና የተመጣጠነ ምግብ አስተዋጽኦ አድርጓል ማለታቸውን የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ምስል ከግብርና ሚኒስቴር
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X