አሜሪካ እና ቻይና የንግድ ማዕቀፍ ስምምነት ላይ ደረሱ - ቤሴንት

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአሜሪካ እና ቻይና የንግድ ማዕቀፍ ስምምነት ላይ ደረሱ - ቤሴንት
አሜሪካ እና ቻይና የንግድ ማዕቀፍ ስምምነት ላይ ደረሱ - ቤሴንት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.10.2025
ሰብስክራይብ

አሜሪካ እና ቻይና የንግድ ማዕቀፍ ስምምነት ላይ ደረሱ - ቤሴንት

የአሜሪካ የግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሴንት፣ ማሌዥያ ውስጥ ለሁለት ቀናት ከተደረጉ ንግግሮች በኋላ እንደተናገሩት፣ አሜሪካ እና ቻይና ለሚቀጥለው የመሪዎች ጉባኤ “በጣም ስኬታማ” የሆነ ማዕቀፍ ላይ ደርሰዋል።

የቻይና ከፍተኛ የንግድ ተደራዳሪ ሊ ቸንግጋንግ እና ምክትል ፕሬዝዳንት ሄ ላይፌንግ በማሌዥያ እየተካሄደ የደቡብ ምሥራቅ እስያ አገራት ማኅበር ጉባኤ ጎን ለጎን ከቤሴንት እና ከንግድ ተወካይ ጄሚሰን ግሪር ጋር እየመከሩ ነው።

እነዚህ ንግግሮች ዶናልድ ትራምፕ ቤጂንግ በብርቅዬ የምድር ማዕድናት እና ቁልፍ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ላይ የኤክስፖርት ቁጥጥርን በማስፋፋቷ ምላሽ ከህዳር 1 ጀምሮ በቻይና ምርቶች ላይ አዲስ 100% ቀረጥ ለመጣል ከዛቱ በኋላ ውጥረቶችን ለማርገብ ያለሙ ናቸው።

ቤሴንት እንደገለጹት፣ ዋይት ሃውስ አዲስ ቀረጥ የመጣል ውሳኔን ትራምፕ እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በደቡብ ኮሪያ ተገናኝተው የንግድ ግጭት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ለመፍታት ጊዜ እንዲያገኙ እስኪደረግ ድረስ ሊያዘገየው ይችላል።

ቻይና ቀደም ሲል የ“እኩል” የንግድ ንግግሮችን ጥሪዋን ደግማለች፤ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጉዎ ጂያኩን “የቀረጥ ጦርነቶች እና የንግድ ጦርነቶች የማንንም ወገን ጥቅም አያገለግሉም” በማለት አጽንኦት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0