'የሕዝብ ዲፕሎማሲ የሩሲያን ዓለም አቀፍ ጥቅሞች ለመጠበቅ ይረዳል 'ሲሉ ፕሬዝዳንት ፑቲን በሞስኮ በተካሄደው 'የጋራ ጥረት ፎረም' ላይ ተናገሩ

ሰብስክራይብ

'የሕዝብ ዲፕሎማሲ የሩሲያን ዓለም አቀፍ ጥቅሞች ለመጠበቅ ይረዳል 'ሲሉ ፕሬዝዳንት ፑቲን በሞስኮ በተካሄደው 'የጋራ ጥረት ፎረም' ላይ ተናገሩ

ፕሬዝዳንቱ በአማካሪያቸው ቫሌሪ ፋዴዬቭ በኩል ባስተላለፉት የጽሑፍ መልዕክት፣ እንዲህ ያለው ዲፕሎማሲ ሩሲያ “ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓትን ለማስፈን ከሚፈልጉ ተመሳሳይ አስተሳሰብ ካላቸው አጋሮችና ተባባሪዎች ጋር ያላትን ትብብር እያጠናከረ ነው” ብለዋል።

ለሕዝብ ዲፕሎማሲ 100ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል የተሰጠው  እና በዛሬው ዕለት የተከፈተው ይህ መድረክ፣ ከ"ከኮመንወልዝ ኢንዲፔንደንት ስቴትስ" (የጋራ ብልጽግና ነጻ አገራት)፣ ከእስያ፣ ከአፍሪካ፣ ከላቲን አሜሪካ እና ከአውሮፓ ከ60 አገሮች የተውጣጡ ከ2 ሺህ በላይ ባለሙያዎችን፣ የሕዝብ ተወካዮችንና ጋዜጠኞችን አሰባስቧል።

ውይይቶቹ በሚከተሉት ላይ ያተኩራሉ፦

🟠 የሕዝብ ዲፕሎማሲ 100ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል፣

🟠 በታላቁ የአርበኝነት ጦርነት ድል 80ኛ ዓመት የመታሰቢያ በዓል፣

🟠 በእጅ አዙር ቅኝ ግዛት እና በናዚአዊነት ላይ የሚደረገው ዓለም አቀፍ ትግል እና

🟠 የሩሲያ ትውፊታዊ፣ መንፈሳዊ እና ሥነ ምግባራዊ እሴቶችን ማስተዋወቅ ናቸው።

ምስል የስፑትኒክ ዘጋቢ

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0