የፑቲን ልዩ መልዕክተኛ በዛሬው ዕለት ከትራምፕ አስተዳደር ጋር ተጨማሪ ስብሰባዎችን ያደርጋሉ ሲሉ ምንጮች ለስፑትኒክ ተናገሩ
12:42 26.10.2025 (የተሻሻለ: 12:44 26.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የፑቲን ልዩ መልዕክተኛ በዛሬው ዕለት ከትራምፕ አስተዳደር ጋር ተጨማሪ ስብሰባዎችን ያደርጋሉ ሲሉ ምንጮች ለስፑትኒክ ተናገሩ
ኪሪል ዲሚትሪቭ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት አስተዳደር ተወካዮች ጋር ጥቅምት 14 እና 15 ስብሰባዎችን ያደረጉ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ውይይት ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ ሲል መረጃ ያለው ምንጭ ለስፑትኒክ ገልጿል።
የመረጃ ምንጩ ከዲሚትሪቭ ጋር ስለ ተገናኙ የትራምፕ አስተዳደር ባለሥልጣናት ተጨማሪ ዝርዝሮችን አልሰጠም።
የሩሲያው ፕሬዝዳንታዊ መልዕክተኛ ከአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር የአሜሪካ እና ሩሲያ የወደፊት ግንኙነት በተመለከ ውይይት ለማድረግ ዓርብ ዕለት አሜሪካ መግባታቸው ይታወሳል ።
ሚዲያዎች እንደዘገቡት ዲሚትሪቭ ከአሜሪካ ልዩ ፕሬዝዳንታዊ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ጋር የሚያደርጉት ስብሰባ በመጪው ቅዳሜ በፍሎሪዳ፣ ማያሚ ሊካሄድ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X