ፕሬዝዳንት ፑቲን ከጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጌራሲሞቭ እና የውጊያ ቡድኖች አዛዦች ጋር ባደረጉት ስብሰባ የተነሱ ተጨማሪ ቁልፍ ነጥቦች

ፕሬዝዳንት ፑቲን ከጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጌራሲሞቭ እና የውጊያ ቡድኖች አዛዦች ጋር ባደረጉት ስብሰባ የተነሱ ተጨማሪ ቁልፍ ነጥቦች
ስለ ዐውደ ግንባሮች ሁኔታ
🟠 "ሴንተር" የውጊያ ቡድን በክራስኖአርሜይስክ እና ዲሚትሮቭ አካባቢ ጠላትን ከቦ ማጠናቀቁን ገራሲሞቭ ገልጿል፡፡
🟠 "ዌስት" (ምዕራብ) የውጊያ ቡድን ኩፒያንስክን ከብቦ፣ በኦስኮል ወንዝ ላይ ያለውን ማቋረጫ ተቆጣጥሮ እና የዩክሬን ወታደሮችን ቡድን መገዱን ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ አስታውቀዋል፡፡
🟠 "ዌስት" የውጊያ ቡድን በዶኔትስክ ሕቦች ሪፐብሊክ ውስጥ ያምፖልን ነፃ ማውጣት እያጠናቀቀ ሲሆን፣ በካርኮቭ ክልል የሚገኘው ቮልቻንስክ 70 በመቶ ነፃ ወጥቷል ሲሉ ጌራሲሞቭ ተናግረዋል፡፡
🟠 እስከ 5,000 የሚደርሱ የዩክሬን ወታደሮች፣ በኩፒያንስክ አካባቢ ሲከበቡ፣ 5,500 የሚሆኑት ደግሞ በክራስኖአርሜይስክ አካባቢ መከበባቸውን ፔስኮቭ ስብሰባውን አስመልክቶ አስተያየት ሲሰጡ ተናግረዋል፡፡
🟠 የሩሲያ ወታደሮች ኩፒያንስክን እና የክራስኖአርሜይስክ-ዲሚትሮቭን ስብስብ በመክበብ ያገኙት ስኬት በሩሲያ ወታደሮች ጀብዱ የተገኘ መሆኑን ፑቲን ገልጸዋል፡፡
🟠 ሩሲያ ሁልጊዜም ከወታደራዊ አስፈላጊነት እንደምትነሳ እና የወታደሮችን ሕይወት የማዳንን ቅድሚያ እንደምትሰጥ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡
ስለ ዩክሬን ምርኮኞች እና ሲቪሎች
🟠 የዩክሬን ኃይሎች ወታደሮቻቸው እጅ ለመስጠት ሲሞክሩ ከጀርባቸው ይመቷቸዋል። ይህም እጅ መስጠትን አስቸጋሪ ያደርግባቸዋል ያሉት ፑቲን፣ ምርኮኞች በሩሲያ እና በዓለም አቀፍ ሕጎች ማዕቀፍ ውስጥ እንዲስተናገዱ አሳስበዋል።
🟠የሩሲያ ጦር በታሪክ የተሸነፈን ጠላት በምህረት እንደሚይዝ እና ይህንንም እንደሚያስቀጥል በማስታወስ፣ የዩክሬን ወታደሮች በሰላም እጃቸውን እንዲሰጡ ለማድረግ ሁሉም እርምጃዎች እንዲወሰዱ ፑቲን መመሪያ ሰጥተዋል።
🟠 ግዛቶች ከዩክሬን ጦር በሚጸዱበት ጊዜ የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ አስተማማኝ አካባቢዎች እንዲጓዙ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል ብለዋል፡፡ የዩክሬን ኃይሎች ሲቪሎችን እንደ ሰው ጋሻ (ጥይት ማብረጃነት) እየተጠቀሙ ነው ሲሉ ፑቲን አስታውቀዋል።
ስለ ተስፋ ሰጪ የጦር መሳሪያዎች እና ስለ 'ቡሬቬስትኒክ' ሚሳኤል
🟠 ፑቲን የስትራቴጂክ አጥቂ ኃይሎችን ሥልጠና አካል በማድረግ ተስፋ የተጣለባቸው የጦር መሣሪያዎች ናሙናዎች ሙከራዎች መደረጋቸውን ሪፖርት አድርገዋል።
🟠 ሥልጠናው የአገሪቱን የኒውክሌር ጋሻ አስተማማኝነት እና የኒውክሌር መከላከያ ኃይሎች ከሌሎች የኒውክሌር አገራት በላቀ ደረጃ ዘመናዊ መሆናቸውን አረጋግጧል።
🟠 የሩሲያው 'ቡሬቬስትኒክ' ሚሳኤል ሙከራ ተጠናቅቋል፡፡ ሚሳኤሎች ልዩ ምርቶች ናቸው፤ ለዓለም ላይ ማንም የለውም፡፡ የሚሳኤል የሙከራ ቁልፍ ግቦችም ተሳክተዋል ሲሉ ፑቲን አስታውቀዋል።
🟠 ጌራሲሞቭ እንደገለፁት፣ "የቡሬቬስትኒክ" ሙከራ ከቀናቶች በፊት በጥቅምት 11 የተካሄደ ሲሆን፣ ሚሳኤሉ 14 ሺህ ኪሎ ሜትሮችን እንደሸፈነ፣ ርቀቱም የመጨረሻ ገደቡ አይደለም፡፡ "ቡሬቬስትኒክ" የሚሳኤል መከላከያ ዘዴዎችን የማለፍ አቅሙን አሳይቷል።
🟠 ፑቲን ሚሳኤሉ በውጊያ ተግባር ከመሰማራቱ በፊት ገና ብዙ ሥራ እንደሚቀረው ገልጸዋል። የሚሳኤሉን ደረጃ እንዲወስኑ፣ ለማሰማራት የሚያስፈልገውን መሠረተ ልማት እንዲያዘጋጁ እንዲሁም ሊሆኑ የሚችሉ የአጠቃቀም ዘዴዎቹን እንዲለዩ ጌራሲሞቭን መመሪያ ሰጥተዋቸዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X