ታይላንድ እና ካምቦዲያ የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ
09:59 26.10.2025 (የተሻሻለ: 10:04 26.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ታይላንድ እና ካምቦዲያ የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ
የታይላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር አኑቲን ቻርንቪራኩል እና የካምቦዲያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሁን ማኔት በትራምፕ ታዛቢነት የሰላም ስምምነቱን ተፈራርመዋል፡፡
ቀደም ብሎ ትራምፕ የታይ-ካምቦዲያ የሰላም ስምምነት ዝርዝሮችን ይፋ አድረገዋል፡፡
የአሜሪካው መሪ የኳላ ላምፑር የሰላም ስምምነቶች ከመፈረሙ በፊት በኩኳ ላምፑር የሚከተሉትን ውሎች ጥቅሰዋል፦
ሁለቱም አገራት ሁሉንም ግጭቶች ለማቆም እና መልካም ጉረቤታዊ ግንኙነት ለመገንባት ተስማምተዋል።
አስራ ስምንት የካምቦዲያ የጦር እስረኞች ይፈታሉ።
ሰላም እንዲሰፍን እና ዘላቂ እንዲሆን ለማረጋገጥ ማሌዥያን ጨምሮ ከደቡብ ምስራቅ እስያ አገራት ማኅበር የተውጣጡ ታዛቢዎች ይሰማራሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X