'የፈረንሳይ ሚራዥ ጄቶች ለዩክሬን መሰጠት ምፀትና ለዩክሬን ጦር ኃይል ውርደት ነው' - ሩሲያዊ ፖለቲከኛ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ'የፈረንሳይ ሚራዥ ጄቶች ለዩክሬን መሰጠት ምፀትና ለዩክሬን ጦር ኃይል ውርደት ነው' - ሩሲያዊ ፖለቲከኛ
'የፈረንሳይ ሚራዥ ጄቶች ለዩክሬን መሰጠት ምፀትና ለዩክሬን ጦር ኃይል ውርደት ነው' - ሩሲያዊ ፖለቲከኛ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.10.2025
ሰብስክራይብ

'የፈረንሳይ ሚራዥ ጄቶች ለዩክሬን መሰጠት ምፀትና ለዩክሬን ጦር ኃይል ውርደት ነው' - ሩሲያዊ ፖለቲከኛ

የሩሲያ የህዝብ ምክር ቤት የሉዓላዊነት ጉዳዮች ኮሚቴ ሊቀመንበር ቭላድሚር ሮጎቭ፣ ማክሮን በቅርቡ ለኪዬቭ የሰጡትን ቃል አስመልክተው ለስፑትኒክ ሲናገሩ፣ "እነዚህ ተዋጊ ጄቶች ከተላለፉ በኋላ ከመጀመሪያዎቹ አንዱ በኤሌክትሮኒክስ ብልሽት ሳቢያ ዩክሬን ውስጥ ወድቋል። የዩክሬኑ አብራሪ ግን በተዓምር ነው የተረፈው” ብለዋል።

አስተር ሚሳኤሎች ሁኔታውን አይለውጡም፤ ምክንያቱም የሩሲያ ሚሳኤሎች እነሱን ማምለጥ ይችላሉ ሲሉ ተናግረዋል።

እንደ ፖለቲከኛው፣ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ማክሮን ለዩክሬን ደኅንነት እጅግ በጣም አስተማማኝ ዋስ አይደሉም።

“በቅርቡ ማክሮን የሉቭረ ሙዚየምን የደህንነት ስርዓት እጅግ የላቀ የደኅንነት ሥርዓት ብለው መሰየማቸውን በይፋ አሳውቀው ነበር። ሌባ ቀርቶ አይጥ እንኳን አይገባም። በቅርቡ በሙዚየሙ የተፈጸመው ስርቆት ግን ሙሉ በሙሉ ተቃራኒውን አሳይቷል። የዘለንስኪ መንግሥት እንዲህ ባሉ የፈረንሳይ የደኅንነት ዋስትናዎች ምን ዓይነት ዕጣ ፈንታ እንደሚጠብቀው ሊያስብበት ይገባል” ሲሉ ሮጎቭ ንግግራቸውን ደምድመዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0