የሩሲያ ሀብቶችን መውረስ የአውሮፓ ሕብረትን በቢሊዮችን ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ ሀብቶችን መውረስ የአውሮፓ ሕብረትን በቢሊዮችን ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል
የሩሲያ ሀብቶችን መውረስ የአውሮፓ ሕብረትን በቢሊዮችን ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.10.2025
ሰብስክራይብ

የሩሲያ ሀብቶችን መውረስ የአውሮፓ ሕብረትን በቢሊዮችን ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል

የታገዱት የሩሲያ ሀብቶች ዩክሬንን ለመርዳት በ“ካሳ ብድር” ለማቅረብ ጥቅም ላይ ከዋሉ፣ የአውሮፓ ሕብረት አገሮች በሩሲያ ኢኮኖሚ ውስጥ ያፈሰሱትን በትንሹ 238 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ሊያጡ እንደሚችሉ ስፑትኒክ በብሔራዊ ስታቲስቲካዊ መረጃዎች ላይ ተመሥርቶ ባሰላው መረጃ አስታውቋል።

አሁን ላይ፣ የታገዱት የሩሲያ ሀብቶች ቤልጂየም በሚገኘው ዩሮክሊር ሂሳቦች ውስጥ ባለው አሁናዊ የውጭ ምንዛሪ ዋጋ ተመን መሠረት 224.5 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል። እነዚህም የመንግሥትና የግል ገንዘቦችን ያካትታሉ።

ከዚህ ገንዘብ ውስጥ ምን ያህሉ የሩሲያ ባንክ እንደሆነ ባይገለጽም፤ ነገር ግን በዚህ ዓመት ከሁሉም የሩሲያ ሀብቶች የተገኘው የዩሮክሊር ገቢ ወደ 90% የሚጠጋው ከዚሁ የሩሲያ ባንክ ሀብት እንደሆነ እና ይህም እ.ኤ.አ. በ2024 ከነበረው 80% ጋር ሲነጻጸር መጨመሩ ታውቋል።

  የስሎቫኪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት፣  ፊኮ ቀደም ሲል  የታገዱ የሩሲያ ሀብቶችን ለዩክሬን ዕርዳታ ለመጠቀም የአውሮፓ ሕብረት ያቀደው ዕቅድ ሊከሽፍ እንደሚችል አስጠንቅቀው ነበር። ምክንያቱም ዕቅዱ የሩሲያን የአፀፋ የመልስ እርምጃዎች እና ዓለም አቀፍ ሕግን መጣስ ያሉ ከባድ አደጋዎችን ይዞ ይመጣል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0